እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ፤” ፩ኛ፡ቆሮ፡፲፩፥፩።
ክርስትናክርስቶስን መምሰልነው። ጌታችን አምላካችንመድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ፡- በወንጌል፡-“እኔን መከተልየሚወድ (ሊመስለኝየሚወድ) ራሱንይካድ፤ (ፈቃደሥጋውን ይተው፥በፈቃደነፍስ ይኑር፥ሥጋ ዊውንዓለም ማለትምሹመቱን ሽልማቱንይናቅ፤) መስቀሉንምተሸክሞ (መከራንሁሉ ታግሶ) ይከተለኝ።”ያለው ለዚህ ነው። ማቴ፡፲፮፥፳፬። በተጨማሪም፡- “ስለ ስሜምቤቶችን ወይምወንድሞችን ወይምእኅቶችን ወይምአባትን ወይምእናትን ወይምሚስትን ወይምልጆችን ወይምእርሻን የተወሁሉ መቶእጥፍ ይቀበላል። (ፍጹም ዋጋአለው)። የዘላለምንምሕይወት ይወርሳል።” የሚል አለ። ማቴ፡፲፱፥፳፱። በመሆኑም፡- ቅዱሳን ስለክርስቶስ ሁሉንትተዋል። “ዓለምንወይም በዓለምያሉትን አትውደዱ፤ በዓለምያለው የሥጋምኞትና የዓይንአምሮት ስለገንዘብም መመካትከዓለም ስለሆነእንጂ ከአባትስላልሆነ፥ ማንም ዓለምንቢወድ የአባትፍቅር በእርሱውስጥ የለም። ዓለሙምምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርንፈቃድ የሚያደርግግን ለዘለዓለምይኖራል።” እያሉ፥ በቃልምበሕ ይወትምሰብከዋል። ፩ኛ ዮሐ፡ ፪፥፲፭። ስለዚህ የዓለም ወዳጅየሆኑና በዓለምምኞት የሚቃጠሉመናፍቃን፥ ከዓለም ፈጽመውበመለየት ክርስቶስንበመሰሉ ቅዱሱንላይ፥ እንደ ተከፈተመቃብር አፋቸውንሲከፍቱ ሊያፍሩይገባ ቸውነበር።
ቅዱሳንዓለምን በመተዋቸው፥ መከራንአጽንታባቸዋለች። ይኸንንም፡- “በዓለም ሳላችሁመከራ አለባችሁ፤ ነገርግን አይዞአችሁ፤ እኔዓለምን አሸንፌዋለሁ።” በማለት፥ ጌታችን አስቀድሞነግሮአቸዋል። ዮሐ፡፲፮፥፴፫። በመሆኑም፡-ጀርባቸው ቆስሎእስኪተላ ድረስተገርፈዋል። የሐዋ፡፭፥፵። በሰንሰለት ታስረው ወደወኅኒ ቤትተወርውረዋል። የሐዋ፡፲፪፥፮። በበትር እየተደበደቡ መከራንመቀበል ብቻሳይሆን፥እግሮቻቸውን ከግንድጋር አጣብቀውጠር ቀዋቸዋል። የሐዋ፡፲፮፥፳፬። በሰይፍገድለዋቸዋል። የሐዋ፡፲፪፥፪። “የሚበልጠውን ትንሣኤእንዲያገኙ (በዕለተምጽአት፡- ብርሃንለብሰው፥ ብርሃን ተጐናጽፈውለመነሣት) እስከሞት ድረስተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻበመሆንና በመገረፍከዚህም በላይበእስራትና በወኅኒተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረውሞቱ፥ ሁሉን እያጡመከራን እየተቀበሉእየተጨነቁ የበግናየፍየል ሌጦ(ቆዳ) ለብሰውዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምናበምድረ በዳናበተራራ፥ በዋሻና በምድርጉድጓድ ተቅበዘበዙ።”ይላል። ዕብ፡፲፩፥፴፭። ጥንተ ጠላታችንዲያብሎስ፡- በአይሁድ፥ በአሕዛብናበመናፍቃን አድሮአሰቃይቶአቸዋል። ተቀዳሚና ተከታይ በሌለውበአንድ ልጁ፥ በኢየሱስክርስቶስ ወደዘለዓለም ክብሩየጠራቸው፥ የጸጋ ሁሉአምላክ እግዚአብሔርግን፥ ከመከራው በኋላ፥ ፍጹማንአድርጐአቸዋል፥አጽንቶአቸዋል፥ አበርትቶአቸዋል። ፩ኛ፡ጴጥ፡ ፭፥፱።
ቅዱሳን፡-የመረጣቸውን አምላክኢየሱስ ክርስቶስንየመሰሉት፥ወንጌልን በማስተማርናተአምራትን በማድረግብቻ ሳይሆን፥ ከላይእንደተገለጠው ጽኑእመከራን በመቀበልምጭምር ነው። ለምሳሌ፡-ጌታችን በመስቀልላይ ሆኖ፥ መከራስላጸኑበት ሰዎች፥“አባትሆይ፥የሚያደርጉትን አያውቁምናይቅር በላቸው፤” ብሎ እንደተናገረ፥ቅዱስ እስጢፋኖስም፡-ጠላቶቹ የድንጋይናዳ እያወረዱበት፥“ጌታ ሆይ፥ይህንኃጢአት አትቁጠርባቸው፤” እያለ በታላቅድምፅ ሲጮኽተሰምቶአል።ሉቃ፡፳፫፥፴፬፣ የሐዋ፡፯፥፷። ሐዋርያውቅዱስ ጳውሎስ፡-“እኔ ክርስቶስንእንደምመስለው እኔንምሰሉ፤ ”በማለትየተናገረው ለዚህነው። ፩ኛ፡ቆሮ፡፲፩፥፩። ምክንያቱም፡- ቅዱሳንን በመምሰልክርስቶስን ወደመምሰል ስለምንደርስነው። በተጨማሪም በሮሜመልእክቱ ላይ፥ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱትእንደ አሳቡምለተጠሩት ነገርሁሉ ለበጐእንዲደረግ እናውቃለን።ልጁ(የባህርይ ልጁኢየሱስ ክርስቶስ) በብዙ ወንድሞችመካከል በኵርይሆን ዘንድ (ለቅዱሳን ሁሉየበጐ ምግባርምሳሌ ይሆናቸውዘንድ) አስቀድሞያወቃቸው (የመረጣቸው) የልጁን (የኢየሱስክርስቶስን) መልክእንዲመስሉ አስቀድሞወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህንደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንምእነዚህን ደግሞአጸደቃቸው፤ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞአከበራቸው።” ብሎአል። ሮሜ፡፰፥፳፰። ከሁሉምበላይ፥ጌታችን አምላካችንመድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ በወንጌል፥ “እኔ የዓለምብርሃን ነኝ፤”ብሎ እንደተናገረ፥“እናንተ የዓለምብርሃን ናችሁ፤”በማለት ተናግሮላቸዋል። ማቴ፡፭፥፲፬፣ ዮሐ፡፰፥፲፪። በመሆኑም፡- ክርስቶስየተቀበላቸውን፥ እርሱንም መስለው የተገኙትንቅዱሳን መቀበል፥ እርሱንመቀበል እንደሆነ ማመንይገባል። ይኸንንም፡-“እናንተንየሚቀበል እኔንይቀበላል፤” በማለትተናግሮላቸዋል። ማቴ፡ ፲፥፵። ኧረ ለመሆኑ፥መናፍቃኑ፡- ቅዱሳኑን ሳይቀበሉ፥ጌታንተቀብለናል፥ የሚሉት በየትበኵል አልፈውነው?
ቅዱሳን፡- በነገር ሁሉእርሱን መስለውበመገኘታቸው፥ ስለ እነርሱመስበክ ማለት፡-ስለ እርሱመስበክ ማለትነው። ምክንያቱም፡-ገድለቅዱሳን የተጻፈው፥ በኢየሱስክርስቶስ ስምስለ ተጋደሉትገድል ነውና። ገድላቸው፡- ኢየሱስ ክርስቶስከእናታቸው ማኅፀንጀምሮ እንደመረጣቸውይናገራል። ይኼንን የመሰለነገር በመጽሐፍቅዱስም ተጽፎይገኛል።ነቢዩ ኤርምያስ፡-“የእግዚአብሔር ቃልወደ እኔእንዲህ ሲልመጣ፡- በሆድሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንምሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥አለኝ።”ብሎአል። ኤር፡፩፥፬። የመላእክት አለቃ ቅዱስገብርኤልም፡- ስለመጥምቀ መለኰትቅዱስ ዮሐንስልደት የምሥራችሲናገር፥“በእናቱማኅፀን ሳለመንፈስ ቅዱስያድርበታል።”ብሎአል። ሉቃ፡፩፥፲፭።ጌታችንአምላካችን መድኃኒታችንኢየሱስ ክርስቶስምበወንጌል፥ “በእናትማኅፀን ጃንደረቦችሆነው የተወለዱ(ከዓለም ተለይተውበድንግልና እንዲያገለግሉትየተመረጡ)አሉ።” በማለት ተናግሮአል። ማቴ፡፲፱፥፲፪። ገድል፡- ቅዱሳን፥ ሁሉን ትተውጌታን እንደተከተሉት ይናገራል። ወንጌልም፡-“ወዲያውም መረባቸውንትተው ተከተሉት።. . .አባታቸውንም ዘብዴዎስንምበታንኳ ላይትተውት ተከትለውትሄዱ።”ይላል። ማር፡፩፥፲፰።ቅዱስጴጥሮስ፡-“እነሆ፥እኛ ሁሉንትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስምን እናገኝይሆን?”ያለውለዚህ ነው። ጌታም፡-“እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስየተከተላችሁኝ በዳግመኛልደት (በመጨረሻዋቀን) የሰውልጅ (በተዋህዶፍጹም ሰውየሆነ የባህርይአምላክ ኢየሱስክርስቶስ) በክብሩዙፋን በሚቀመጥበትጊዜ፥እናንተ ደግሞበአሥራ ሁለቱየእስራኤል ነገድ(በእስራኤል ዘሥጋበአይሁድ፥ በእስራኤል ዘነፍስ በምዕመናን) ስትፈርዱ በአሥራሁለት ዙፋንትቀመጣላችሁ።”ብሎታል። ማቴ፡፲፱፥፳፯። በዚህም፡- የባህርይ ፈራጅኢየሱስ ክርስቶስ፥ እነርሱንየጸጋ ፈራጅአድርጐ ራሱንአስመስሎአቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ፡-“በአጭርቃል በእናንትመካከል ዝሙትእንዳለ ይወራል፤የዚያምዓይነት ዝሙትበአሕዛብስ እንኳየማይገኝ ነው፥ የአባቱንሚስት ያገባሰው ይኖራልና። እናንተምታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን?ይህን ሥራየሠራው ከመካከላችሁይወገድ። እኔ ምንምእንኳ በሥጋከእናንተ ጋርባልሆን በመንፈስከእናንተ ጋርነኝ፥ ከእናንተምጋር እንዳለሁሆኜ ይህንእንደዚህ በሠራውላይ በጌታችንበኢየሱስ ክርስቶስስም አሁንፈርጄበታለሁ።”ያለውለዚህ ነው። ፩ኛ፡ቆሮ፡፭፥፩።
በአጠቃላይአነጋገር፥ ገድል፡-ቅዱሳን፡- በኢየሱስ ክርስቶስስም እንዳስተማሩ፥በስሙመከራ እንደተቀበሉናድንቅ ድንቅተአምራትን እንዳደረጉ፥ በመጨረሻምቃል ኪዳንእንደተሰጣቸውና በሰማዕትነትእንደ አለፉይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስምበቅዱሳን ትምህርት፥ ገድልናተአምራት የተሞላነው። ለምሳሌ፡-ቅዱስሉቃስ፡-ቅዱሳንሐዋርያት፥ኢየሱስ ክርስቶስንስለ መሰሉበትገድል፥“ሐዋርያትንምወደ እነርሱጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስምስም እንዳይናገሩአዝዘው ፈቱአቸው። እነርሱምስለ ስሙይናቁ ዘንድየተገባቸው ሆነውበመገኘታቸው ከሸንጐው ፊትደስ እያላቸውወጡ፤ ዕለት ዕለትምበመቅደስና በቤታቸውስለ ኢየሱስእርሱ ክርስቶስእንደ ሆነማስተማርንና መስበክንአይተዉም ነበር።” በማለት ጽፎአል። የሐዋ፡፭፥፵። የተአምርመጽሐፋቸውም ሲነበብየሚሰብ ከውኢየሱስን ነው።“ጴጥሮስ ግን፡- ወርቅና ብርየለኝም፤ ይህን ያለኝንግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱበኢየሱስ ክርስቶስስም ተነሥናተመላለስ አለው። በቀኝእጁም ይዞአስነሣው፤ በዚያን ጊዜምእግሩና ቍርጭምጭሚቱጸና፤”ይላል።የሐዋ፡፫፥፮። ስለ ቅዱስጳውሎስም፡- ኤልማስየተባለውን ጠንቋይበገሠጸው(በፈረደበት) ጊዜ፥ስለሆነው ነገር፥“ጳውሎስ የተባለውሳውል ግንመንፈስ ቅዱስንተሞልቶ ትኵርብሎ ሲመለከተው፡- አንተ ተንኰልሁሉ ክፋትምሁሉ የሞላብህየዲያብሎስ ልጅ፥የጽድቅም ሁሉጠላት፥የቀናውን የጌታንመንገድ (ወንጌልን) ከማጣመም አታርፍምን? አሁንም እነሆ፥የጌታ እጅበአንተ ላይናት፥ ዕውርም ትሆናለህ፥ እስከጊዜውም ፀሐይንአታይም አለው።ያንጊዜም ጭጋግናጨለማ ወደቀበት፥በእጁምየሚመራውን እየዞረፈለገ።” የሚልተጽፎአል። የሐዋ፡፲፫፥፱። በተጨማሪም፥“እግዚአብሔርም በጳውሎስእጅ የሚያስገርምተአምራት ያደርግነበር፤ስለዚህም ከአካሉጨርቅ ወይምልብስ ወደድውዮች ይወስዱነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸውነበር፥ ክፉዎች መናፍስትምይወጡ ነበር።”የሚል አለ።የሐዋ፡፲፱፥፲፩። ቅዱስ ጴጥሮስም፡- በሐናንያናበሰጲራ ፈርዶባቸዋል።“ሐናንያ ሆይ፥መንፈስቅዱስን ታታልልናከመሬቱ ሽያጭታስቀር ዘንድሰይጣን በልብህስለ ምንሞላ? ሳትሸጠውየአንተ አልነበረምን? ይህን ነገርስለ ምንበልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂሰውን አልዋሸህምአለው። ሐናንያም ይህንቃል ሰምቶወደቀ ሞተም፤. . .ከሦስት ሰዓትያህል በኋላምሚስቱ የሆነውንሳታውቅ ገባች። ጴጥሮስምመልሶ፡- እስቲንገሪኝ፥ መሬታችሁን ይህንለሚያህል ሸጣችሁትን? አላት። እርስዋም፡- አዎንይህን ለሚያህልነው አለች። ጴጥሮስም፡- የጌታን መንፈስትፈታተኑ ዘንድስለ ምንተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽንየቀበሩት ሰዎችእግር በደጅነው፥ አንቺንምያወጡሻል አላት። ያንጊዜም በእግሩአጠገብ ወደቀችሞተችም፤”ይላል። የሐዋ፡፭፥፩። ከዚህም፡- በቅዱሳን ላይበድፍረት መናገር፥ በእግዚአብሔርላይ መናገርእንደሆነ ትምህርትእንወስዳለን። እንግዲህ የቅዱሳን ገድልናተአምር የሚባለውይኸንን የመሰለመሆኑን በሚገባእናስተውላለን።በመሆኑም ነገረ ቅዱሳንየጌታን ስምይበልጥ ይገልጠዋልእንጂ አይሸፍነውም። ምክንያቱም፡- እነርሱ በሕይወታቸውየኢየሱስ ክርስቶስንስም እንዲሸከሙየተመረጡ ናቸውና። ይኸንንም፡- የጌታችን ቃል፥“ይህ በአሕዛብምበነገሥታትም በእስራኤልምልጆች ፊትስሜን ይሸከምዘንድ ለእኔየተመረጠ ዕቃ(መሣሪያ)ነውና።” በማለት ይነግረናል። ከዚህምበላይ ቅዱሳንየጸጋ አማልክት(ገዢዎች) ናቸው። እግዚአብሔርሙሴን፡- “እይ፥እኔለፈርዖን አምላክአድርጌሃለሁ።” ማለቱየሚያረጋግጥልን የኼንኑነው። ዘጸ፡፯፥፩።በአዲስ ኪዳንም ኢየሱስክርስቶስ፡- ቅዱሳንየጸጋ አማልክትመሆናቸውን ጠቅሶሰብኰአል። መዝ፡፹፩፥፮፣ ዮሐ፡፲፥፴፬። እንግዲህ መናፍቃኑ፡- የሚያዋጣቸውከሆነ፥“ለምንእንዲህ አደረግህ?” ብለው እርሱን ይጠይቁት።
ቅዱሳንንመቃወም እኮየሰይጣን ሥራነው።“ባላጋራችሁዲያብሎስ የሚውጠውንአጥቶ እንደሚያገሣአንበሳ ይዞራልና፤” የተባለው ለዚህነው። ፩ኛ፡ጴጥ፡፭፥፰። በራእየ ዮሐንስም ላይ፥“ አሁን የአምላካችንማዳንና ኃይልመንግሥትም የክርስቶስምሥልጣን ሆነ፥ቀንናሌሊትም በአምላካችንፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን (የቅዱሳን) ከሳሽ ተጥሎአልና።እነርሱምከበጉ (ከአዲስኪዳን በግከኢየሱስ ክርስቶስ) ደም የተነሣከምስክራቸውም ቃልየተነሣ ድልነሡት፥ ነፍሳቸውንም (ሰውነታቸውንም) እስከ ሞትድረስ አልወደዱም። ስለዚህሰማይና በውስጡየምታድሩ ሆይ፥ደስይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕርወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂትዘመን እንዳለውአውቆ በታላቅቍጣ ወደእናንተ ወርዶአልና።” የሚል አለ። ራእ፡፲፪፥፲። መጽሐፈ(ገድለ) ኢዮብንብንመለከት፡- “እግዚአብሔርሰይጣንን፡-ከወዴትመጣህ? አለው። ሰይጣንም፡- በምድር ላይዞርሁ፥ በእርስዋም ተመላለስሁብሎ ለእግዚአብሔርመለሰ። እግዚአብሔርም ሰይጣንን፡- በውኑባሪያዬን ኢዮብንተመለከትኸውን? በምድርላይ እንደእርሱ ፍጹምናቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀሰው የለም፤ በከንቱምአጠፋው ዘንድአንተ ምንምብታንቀሳቅሰኝ እስከአሁን ፍጹምነትንይዞአል።”ይላል። ኢዮ፡፪፥፪። ሰይጣንአይቻለውም እንጂቢቻለው፥ እግዚአብሔርን እንኳ በቅዱሳንላይ ማነሣሣትይፈልጋል። በትንቢተ ዘካርያስላይ ደግሞ፡-“እርሱም ታላቁንካህን ኢያሱንበእግዚአብሔር ፊትቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንምይከስሰው ዘንድበቀኙ ቆሞነበር።እግዚአብሔርም ሰይጣንን፡- ሰይጣን ሆይ፥እግዚአብሔር ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምንየመረጠ እግዚአብሔርይገሥጽህ፤ በውኑ ይህከእሳት የተነጠቀትንታግ አይደለምን? አለው። ኢያሱምአድፋም ልብስለብሶ በመልአኩፊት ቆሞነበር።እርሱም መልሶበፊቱ የቆሙትን፡-እድ ፋሙንልብስ ከእርሱላይ አውልቁ፥አላቸው። እርሱንም፡- እነሆ፥አበሳህን ከአንተአርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስምአለብስሃለሁ አለው። ደግሞ፡-ንጹሕ ጥምጥምበራሱ ላይአድርጉ አለ። እነርሱምበራሱ ላይንጽሕ ጥምጥምአደረጉ፥ልብሱ ንምአለበሱት፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡነበር።” ይላል። ዘካ፡፫፥፩። ከዚህምየቅዱሳን ከሳሾችየሰይጣንን ሥራእየሠሩለት እንደሆነ፥ የእግዚአብሔርምተግሣጽ እንደወደቀባቸውእንረዳለን። በሌላ በኵልደግሞ፥ መናፍቃን ከሰይጣንጋር ተሰልፈው፥ ያላቸውንጥላቻ ሁሉቢገልጡ፥ ቅዱሳንን ከክብራቸውዝቅ ማድረግእንደማይችሉ እንማራለን። ቅዱስጳውሎስ፡-“እግዚአብሔርየመረጣቸውን (የተመረጡቅዱሳንን) ማንይከሳቸዋል?” ያለውለዚህ ነው። ሮሜ፡፰፥፴፫።
0 comments:
Post a Comment