የጋዜጣው ጽሑፎች፣ «መንፈሳዊ ኮሌጆቹ በአጠቃላይ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው» አይሉምበጋዜጣው አጻጻፍ አንዳንድ የቃላት አጠቃቀሞች ላይ ቅሬታ ካለ ለመወያየት ዝግጁዎች ነንጉዳዮቹን እንድናስረዳና የተፈጠረውንም ችግር ለመረዳት የውይይት መድረክ ይዘጋጅልንበተለያየ መንገድ እንደጠየቅነው፣ በአካል የመወያያ ዕድል ማጣታችን በእጅጉያሳዝነናል ለሚታረም ነገር እርምት መውሰድና ስናጠፋም ይቅርታ መጠየቅየአገልግሎታችን መርሕ ነው
* * *
ሰዎች እንደመኾናችንና ልንሳሳት ስለምንችል፣ በማንኛውም ደረጃ ተወያይተን የሚታረም ነገር ካለ አስፈላጊውን እርምት መውሰድ እና በትክክል ጥፋት እንዳጠፋንም ስንረዳ ይቅርታ መጠየቅ አንዱና ዋነኛው የአገልግሎታችን መርሕ ነው፡፡በሀገራችን የተከሠቱትን ማኅበራዊችግሮች ለመፍታት ኹሉም አካል በየዘርፉበሚረባረብበት በዚኽ ወቅት፣ ትልቅሓላፊነት ያለባት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንአባትና ልጆች እንዲህ ዓይነት ደብዳቤዎችንበመጻጻፍ መጠመዳችን በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ሕግ አውጥቶ፣ ሥርዓት ሠርቶ የሰጠን የቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በማኅበሩ አገልግሎቶች ላይ አኹንም እየተፈጠሩ ያሉት ዕንቅፋቶች እንዲታዩልንና አስፈላጊው እርምት እንዲደረግልን በታላቅ ትሕትናናአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከዚኽ በታች ይመልከቱ)
0 comments:
Post a Comment