2. የሥርዓተ ምንኩስና ታሪክ
2.1 - አባ ጳውሊ እና አባ እንጦንስ
2.1.1- አባ ጳውሊ
አባ ጳውሊ እና አባ እንጦንስ
በተባሕትዎ መኖር ከጥንት ዘመን የመጣ ይሁንእንጂ የብሕትውናን ኑሮ ሥርዓት በወጣለት መልኩየጀመረው አባ ጳውሊ የተባለው ግብፃዊ አባት ነው፡፡በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት በክርስቲያኖችላይ በተነሣው ስደት ምክንያት አባ ጳውሊና ቆይቶምደግሞ ሌሎች የአካባቢው ክርስቲያኖች በግብፅበረሃዎች ውስጥ በምናኔ ይኖሩ ነበር፡፡
ይህንን አባ ጳውሊ የጀመረውን ሥርዓት አጠናክሮለማስፋፋት ያበቃው ደግሞ አባታችን አባ እንጦንስነው (251-356ዓ.ም.)፡፡
2.1.2- አባ እንጦንስ
አባ እንጦንስ ግብፅ ውስጥ ቆማ በተባለች መንደርከሀብታም ቤተሰቦች በ251 ዓ.ም ተወለደ፡፡ወዳጆቹገና የ2ዐ ዓመት ወጣት እያለ ስላረፉበማቴ.19÷21 ላይ ያለውን ትምህርት መሠረትአድርጐ የወረሰውን ሀብት በሙሉ በመሸጥለድኾች አከፋፈለና ወደ ግብፅ በረሃ በመውረድለ85 ዓመት በተጋድሎ ኖሯል፡፡
የአባ እንጦንስ ዓላማ ከሰው ርቆ በብሕትውናበበረሃለመኖር ነበር፡፡ ነገር ግን ተአምራቱን የሰማውሕዝብ ከግብፅ ብቻ ሳይሆን ከመካከለኛውምሥራቅና ከአውሮፖ ምድር ሳይቀር ወደ በአቱይጐርፍ ጀመር፡፡ በኋላም በሕይወቱ የተማረኩባሕታውያን በዙሪያው ባሉ ዋሻዎች መኖር ጀመሩ፡፡
የአባ እንጦንስን የሕይወት ታሪክ የጻፈለት አባታችንአትናቴዎስ ሲሆን አትናቴዎስም ሥርዓተ ምንኩስናንየተቀበለው ከዚሁ አባት ነው፡፡ ታላቁ ንጉሥቆስጠንጢኖስም ዝናውን በመስማቱ «በጸሎትህአስበኝ» በማለት ደብዳቤ ጽፎለት እንደነበር ታሪኩይናገራል፡፡
አባ እንጦንስ ለ85 ዓመታት በብሕትውና ሲኖርከበኣቱ የወጣው ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡የመጀመሪያው በንጉሥ መክስምያኖስ ትእዛዝስደትና መከራ የደረሰባቸውን ክርስቲያኖችንለማፅናናት በመላዋ ግብፅ በ311 ዓ.ም. ያደረገውጉዞ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አርዮሳውያን በቅዱስአትናቴዎስ ላይ በተነሡበትጊዜ ለመንፈስ አባቱለሐዋርያዋው አትናቴዎስና ለንጽሕት ተዋሕዶእምነቱ ያለውን ቆራጥነት በመግለጥ ሕዝቡንለማጽናት በ338 ዓ.ም ደቀ መዛሙርቱን አስከትሎየተጓዘው ሐዋርያዊ ጉዞ ነው፡፡
የባሕታውያኑ በአባ እንጦንስ ዙሪያ መሰባሰብለማኅበር ጸሎት፣ ከዘራፊዎች ለመጠበቅና የደከሙአበውን ለመርዳት አስችሏቸዋል፡፡ በዚህምየመጀመሪያው የገዳማውያን የማኅበር ኑሮተጀመረ፡፡
አባ እንጦንስ የመነኮሳቱ ልብስ ነጭ ፈረጅያና ቆብ፣መታጠቂያቸውም ከቆዳ የተሠራና ሠቅ እንዲሆንወስኖ ነበር፡፡
መነኮሳቱ ሳምንቱን በየበኣታቸው ሲጾሙና ሲጸልዩሰንብተው እስከ እሑድ ምሽት ድረስ ደግሞ በአባእንጦንስ ዋሻ ዙሪያ ተሰባስበው ሲጸልዩና ሥርዓተአምልኮ ሲፈጽሙ ይውሉ ነበር፡፡ አባ እንጦንስ በዚህሁኔታ ሥርዓተ ምንኩስናን አስፋፍቶ በተወለደበ105 ዓመቱ ዐርፎአል፡፡አባ ጳውሊ የጀመረውንሥርዓተ ምንኩስና አጠናክሮ ያስፋፋው አባእንጦንስ ነው፡፡
2.2 አባ ጳኩሚስ
በሥርዓተ ምንኵስና ታሪክ ሌላውን ታላቅ ሥፍራየያዘው ደግሞ የአባ እንጦንስ ደቀ መዝሙርየነበረው አባ ጳኩሚስ ነው (23ዐ-346 ዓ.ም.)፡፡ አባጳኩሚስ ግብፅ ውስጥ ኤስና በምትባል መንደርከአረማውያን ቤተሰቦች በ29ዐ ዓ.ም. ተወለደ፡፡በቆስጠንጢኖስ ዘመነ መንግሥት ለውትድርናምተመልምሎ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በውትድርናውዘመን የክርስቲያኖችን ቆራጥነት፣ደግነትና ርኀራኄበማየቱ ልቡ ስለተነካ ግዳጁን ፈጽሞ ሲመለስበ313 ዓ.ም. የክርስትናንእምነት ጠንቅቆ በመማርአምኖ ተጠመቀ፡፡
የአባ ጳኩሚስ ልቡና የቅዱስ እንጦንስ ደቀመዝሙር በነበረው በአባ ጴላጦንስ ኑሮስለተማረከወደ በረሃ ወርዶ የብሕትውናን ኑሮናሥርዓት ሲማር ከቆየ በኋላ በ32ዐ ዓ.ም. በዓባይወንዝ አጠገብ ታቤኒስ ከተባለው ቦታ የራሱን ገዳምመሠረተ፡፡ በዙሪያው ለተሰበሰቡት መነኰሳትምየአንድነት ኑሮ ሕግ አወጣላቸው፡፡በአባ እንጦንስለተጀመረው የማኅበረ መነኰሳት ኑሮየተጠናከረሥርዓት አውጥቶ የበለጠ ከማስፋፋቱምበተጨማሪ ዘጠኝ የወንድና ሁለት የሴቶች ገዳማትመሥርቷል፡፡
አባጳኩሚስ ያወጣው የመነኰሳት የአኗኗር ሕግ ዋናውቅጂ ሲጠፋ ወደ ላቲን የተተረጐመው ግን እስከዛሬድረስ ይገኛል፡፡ ከሕግጋቱ መካከል፡-
መነኮሳት ጠዋትና ማታ በማኀበርእንዲጸልዩ፣
በኀብረት በአንድነት እንዲሠሩ፣
ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትረውእንዲመለከቱ፣
የቁም ጽሕፈት እንዲማሩ፣
ገቢና ወጪአቸው አንድ ላይ እንዲሆን፣
በአንድነት እንዲመገቡ፣
አንድ ዓይነት ልብስ እንዲኖራቸው፣
ንጽሕ ጠብቀው እንዲኖሩ፣
ደግነት፣ ፍቅርና ታዛዥነትእንዲኖራቸው፣የሚሉት ይገኙበታል፡፡
አንድ ሰው ወደ ገዳማቱ ሲመጣ የሦስት ዓመትአመክሮ ይሰጠውና ጠባዩና ፍላጐቱ ይገመገማል፡፡ከዚያ በኋላም ብርታቱና ጽናቱ ታይቶ ወደ ማኅበረመነኰሳቱ ይቀላቀላል፡፡ አባ ጳኩሚስ በዚሁ ዓይነትመንገድ ሥርዓት ሠርቶ ሕግ አጽንቶ ገዳማትንካስፋፋ በኋላ በተወለደ በ56 ዓመቱ በ346 ዓ.ም.ዐረፈ፡፡
3. ሥርዓተ ምንኵስናን በሌላው ዓለምያስፋፉ አበው
3.1 አትናቴዎስ ሐዋርያዊው (295-373 ዓ.ም.)
አትናቴዎስ ሐዋርያዊው
ቅዱስአትናቴዎስ ከታላቁ ርዕሰ ገዳማውያን ከአባእንጦንስ ዘንድ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምሮፈጽሟል፡፡ የአባ እንጦንስን የሕይወት ታሪክ (ገድል)የጻፈውም እርሱ ነው፡፡ አርዮሳውያን በቅዱስአትናቴዎስ ላይ በግፍ በተነሡበት ጊዜ ወደ ሮምበመሰደድ ከ339-346 ዓ.ም. ተቀምጧል፡፡ የሮምክርስቲያኖች አትናቴዎስና ተከታዮቹ የለበሱትንየመነኰሳት ልብስና ቆብ ተመልክተውተገረሙ፡፡እርሱም በቆየባቸው ሰባት ዓመታት ከአባ እንጦንስየተማረውን የመነኰሳት ሕግና አኗኗርአስተምሯቸዋል፡፡ በሮማ ምድርም ሥርዓተምንኩስናን ለማስፋፋት የመጀመሪያው አባትአትናቴዎስ ሐዋርያዊ ነው፡፡
3.2 ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ (330-379 ዓ.ም)
ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ
ባስልዮስ በግብፅ ገዳማት በብሕትውና ከቆየ በኋላከ36ዐ ዓ.ም. ጀምሮ በታናሽ እስያ (ዛሬ ቱርክበሚባለው አካባቢ) የምነናን ኑሮ በመመሥረትዛሬየግሪክ፣ ሩሲያ፣ ወዘተ. አብያተ ክርስቲያናትየሚገለገሉበትን የመነኰሳት ሕግ ያወጣው እርሱነው፡፡
3.3 ዮሐንስ ካስያን (360-435 ዓ.ም.)
ግብፅ ውስጥ በቴብያድና ጥቂት ዓመታትበብሕትውና ከቆየ በኋላ ወደ ፈረንሳይ በመመለስበ415 ዓ.ም. በፈረንሳይማርሴይ አጠገብ ሁለትገዳማትን መሠረተ፡፡ በግብፅ ያጠናውን ሥርዓተመነኰሳት መሠረት አድርጐ ሁለት መጻሕፍትንምአዘጋጅቷል፡፡
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ በአባ ጳውሊ የተጀመረውየምንኵስና ሕይወት በመላው ዓለም ሊስፋፋናወደሀገራችንም ለመድረስ በቅቷል፡፡የመጀመሪያውን የሴቶች ገዳም የመሠረተችውደግሞ የአባ ጳኩሚስ እኀት ማርያም ነች፡፡
ምንኵስና በኢትዮጵያ
ይቀጥላል - ይቆየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቢ
1. ትንሣኤ ቁ.99/1978
2. ገድለ አባ ሊባኖስ
3. ገድለ አባ ዮሐንስ
4. ዜና መንዝ
5. የአንኰበር መሳፍንት የታሪክ መጽሐፍ
6. ትንሣኤ ቁ.11/79
7. ትንሣኤ ቁ.22/80
8. Conti Rossini, steria PL.XLIV
9. ሉሌ መላኩ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አ.አ1986
10. አባ ጎርጎርዮስ፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለምመድረክ
11. አባ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንታሪ
ሐመር መጽሔት
ምንጭ: http://www.melakuezezew.info/
0 comments:
Post a Comment