- «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋነው፡፡
- መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለውግሥ ይሆናል፡፡
- «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትንያመለክታል፡፡
- «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንበየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስትክፍል አለው፡፡
1) አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ይህም ማለት ተዘክሮተእግዚአብሔር ነው፡፡
2) ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርንመስማትና በንስሐ እየታደሱበሕይወት መኖር ነው፡፡
3) ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜውየሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
4) አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስበገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድልአድርጎ መነሣት ነው፡፡
5) ዐምስተኛውና የመጨረሻው«የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይአምላክ የጌታችን የመድኀኒታችንኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ»መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ»ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርናለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔበአንድነት የሚነሣው የዘለዓለምትንሣኤ ይሆናል፡፡
ወደተነሣንበት ዐላማ ስንመለስ የትንሣኤበዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱምስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ«ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡
«ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ«ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ»ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት =ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣እየተቸኮለ የሚበላ መሥዋዕት፣ መሻገርመሸጋገር ማለት ነው፡፡ ነጮቹበእንግሊዝኛው «ስኦቨር» ይሉታል የዚህምታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበርየነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነትየተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹምደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል«ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡
ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስእስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናነ ክርስቶስትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖበእርሱ ትንሣኤ
ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፣
ከኃሳር ፤ ከውርደት ወደክብር፣
ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደዘለዓለማዊ ነፃነት፣
ከአደፈ፣ ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወትወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበትታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡
- ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖይታያል፡፡
- መድኀኒታችን ሞትን በሞቱ ድል መትቶ፣ስሙና መቃብርን አጥፍቶ በሥልጣኑየተነሣው መጋቢት 29 ቀን በ34 ዓ.ምእንደሆነ ታሪከ ቤተ ከርስቲያን ያስረዳል፡፡
- የትንሣኤ በዓል መከበር የጀመረውበቅዱሳን ሐዋርያትና በሰብዐ አርድእት፣ኋላም በየጊዜው በተነሡት ተከታዮቹምእመናን ነው፡፡ ድምቀቱና የአከባበርሥርዐቱ ይበዛ ይቀነስ እንደሆን እንጂመከበሩ ተቋርጦ አያውቅም፡፡
«እንኳንለብርሃነትንሣኤውአደረሰን»
ከትንሣኤ እሑድ ቀጥለው ያሉት ዕለታትሰሙነ ፋሲካ ወይም ትንሣኤ እየተባሉየየራሳቸው ምስጢራዊ ስያሜ አላቸው፡፡ይኸውም፡-
ሰኞ
ጌታችን በሞትና ትንሣኤው ነፍሳትን ከሲኦልአውጥቶ ወደ ገነት አሻግሮ ለማስገባቱመታሰቢያ ሆና «ፀአተ ሲኦል ማዕዶት»ትባላለች፡፡ ዮሐ. 19-18 ሮሜ. 5-10-17የዳግም ትንሣኤው ማግሥት ያለችው ግንገበሬው፤ ወንዶቹ እርሻ ቁፋሮውን፣ ንግዱን፣ተግባረ እዱን ሁሉ ሴቶቹ ወፍጮውን፣ፈትሉን፣ ስፌቱን የሚጀምሩባት ዕለትስለሆነች «እጅ ማሟሻ» ሰኞ ትባላለች፡፡
ማክሰኞ
የትንሣኤው ዕለት እሑድ ማታ ጌታችንበዝግ ቤት ገብቶ ለሐዋርያት ሲገለጽ ቶማስሐዋርያ አልነበረም ኋላ ከሔደበት ሲመጣሌሎቹ ሐዋርያት ትንሣኤውን ቢነግሩት እኔሳላይ አላምንም በማለቱ በዚህ ጥያቄውመሠረት በሳምንቱ ጌታችን በድጋሚስለተገለጸ ለዚህ መገለጹ መታሰቢያ ሆናዕለቲቱ «በቶማስ» ተሰየመች፡፡ ዮሐ. 20-24-30
ረቡዕ
ከሞተና ከተቀበረ አራት ቀን በኋላከመቃብር ጠርቶ ላሥነሣው፣ አላዓዛርመታሰቢያ የእርሱንም ተነሥቶ በማየትበጌታችን ብዙ ሕዝብ ስለአመነበት ቀኒቱ«አልዓዛር» ተብላ ትታሰባለች፡፡ ዮሐ. 11-38-46
ኃሙስ
የአዳም ተስፋው ተፈጽሞለት ከነልጅ ልጆቹወደቀደመ የገነት ክብሩ ለመግባቱመታሰቢያ ሆና «የአዳም ኀሙስ» ተብላይኸው ትከበራለች፡፡ ሉቃ. 24-25-49
ዐርብ
በክርስቶስ ደም ተዋጅታ በተመሠረተችውቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያበመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዐርብ«ቤተ ክርስቲያን» ተብላ ትጠራለች፡፡ ማቴ. 26-26-29 የሐ. ሥራ. 20-28 ይህችዕለትም እንደ ዕለተ ኀሙስ ሦስት ስያሜዎችአሏት፡፡ ይኸውም እንደኛው ከሆሳዕና ቅዳሜበፊት ያለችው ዐርብ የጌታችን አርባው ጾምየሚፈጸምባት የጾመ ድጓው ቁመትምየሚያበቃባት፣ በመሆኗ በቤተ ክርስተያን«ተጽዒኖ» ስትባል በሕዝቡም ዘንድበሕማማትና ሰሙነ ትንሣኤው ከባዱን ሥራስለሚያቆምባት «የወፍጮ መድፊያ፣የቀንበር መስቀያ» ትባላለች፡፡
- ሁለተኛውም በመጀመሪያ የሰው አባትናእናት አዳምና ሔዋን ስለተፈጠሩባት፣ ኋላምበሐዲስ ኪዳን ጌታችን ለቤዛ ዓለም መከራተቀብሎ ስለተሰቀለባትና የማዳን ሥራውንስለፈጸመባት «ዕለተ ስቅለት አማናዊቷዐርብ» ትባላለች፡፡
- ሦስተኛውም ይኸው በሰሙነ ትንሣኤውያለችው ደግሞ «ቤተ ክርስቲያን» ትባላለችማለት ነው፡፡
ቀዳሚት
በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡከአንዳንዱ በስተቀር ገበያ እንኳንስለማይገበይባት «የቁራ ገበያ» የገበያጥፊያ ስትባል በቤተ ክርስቲያን ግን በዘመነሥጋዌው በገንዘባቸውና ጉልበታቸውለአገለገሉት በስቅለቱ ዋይ ዋይ እያሉ እስከቀራንዮ ለተከተሉት፣ የትንሣኤው ዕለት ገናከሌሊቱ ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘውበመገሥገሣቸው ትንሣኤው ከሁሉ ቀድሞለተገለጸላቸው ቅዱሳት አንስት መልካምመታሰቢያ ሆና «አንስት» ተብላ ትጠራለች፡፡ሉቃ. 23-27-33፣ 24-1-01፣ ማቴ. 25-1-11
የዋናው ትንሣኤ ሳምንት እሑድ...« ዳግም ትንሣኤ »
በዚች ሰንበት ከላይ እንደተጠቆመውየትንሣኤው ዕለት ጌታችን ለቅዱሳንሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸውተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎምትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስአልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣየጌታችንን መነሣትና እንደተገለጸላቸውበደስታ ሲነግሩት «በኋላ እናንተ ዐየንብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን«ሰምቼአለሁ» ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር?አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም»በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንምየመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰንየሌለው የባሕርይ አምላክ መድኀኔዓለምክርስቶስ ልክ እንደመጀመሪያው ትንሣኤዕለት አበው ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤትእንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ «ሰላምለሁላችን ይሁን» በማለት በመካከላቸውቆመ፤ ቶማስንም «ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪአትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣የተወጋ ጐኔንም ናና እይ» ብሎ አሳየው፡፡እርሱም ምልክቱን በማየቱ በመዳሰሱትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱበመረዳቱ «ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ»አመነ፡፡
- እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢርለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበትዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡ ዮሐ. 20-24-30
ወስብሐትለእግዚአብሔር
.
0 comments:
Post a Comment