• በቅርብ የተጻፉ

    Thursday 24 March 2016

    ሰበር ዜና – ዐውደ ርእዩ በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዳይካሔድ የተከለከለው በመንግሥት ትእዛዝ ነው፤ “ላልተሟሉት ቅድመ ኹኔቻዎች” ማዕከሉ ሓላፊነቱን ወስዷል

    ፈቃዱን ለመስጠት ይመለከተዋል የተባለው የአዲስ አበባ አስተዳደር፣“ለዐውደ ርእይ ፈቃድ የመስጠት አሠራር የለኝም፤ በእንግዳ ሕግ ፈቃድ ለመስጠት አልችልም፤” ብሏል፡፡ “ዝግጅቱን ለማካሔድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ኹኔታዎችን በተሟላ መልኩ ኤግዚቢሽን ማዕከሉ ለአዘጋጆች ባለመግለጹና እንዲያሟሉ ባለማስቻሉ ዝግጅቱ በተያዘለት ፕሮግራም ሊካሔድ አልቻለም፡፡”/ማዕከሉ/በተፈጠረው ክፍተት ላይ ከማኅበሩ ጋር ተከታታይና ሰላማዊ ውይይት ማድረጉን የገለጸው ማዕከሉ፥ “ለማኅበረ ቅዱሳን፣ ለተሳታፊዎችና ለተመልካቾች ከፍተኛ ይቅርታ ይጠይቃል፤” በማለት የይቅርታ መልእክቱን በተለያዩ ብዙኃን መገናኛዎች እያስተላለፈ ነው፡፡
    የማኅበሩ ጽ/ቤት፣ የዐውደ ርእዩን ተለዋጭ ቦታ እና ጊዜ ገና አልወሰነም፡፡ጋዜጣዊ መግለጫው፣ በዋናው ማእከል ጽ/ቤት በዋና ጸሐፊው እየተሰጠ ነው፡፡

    • የተሰጡ አስተያየቶች
    • በፌስቡክ (Facebook) የተሰጡ አስተያየቶች

    0 comments:

    Post a Comment

    Item Reviewed: ሰበር ዜና – ዐውደ ርእዩ በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዳይካሔድ የተከለከለው በመንግሥት ትእዛዝ ነው፤ “ላልተሟሉት ቅድመ ኹኔቻዎች” ማዕከሉ ሓላፊነቱን ወስዷል Rating: 5 Reviewed By: Getahun Amare - ጌታሁን አማረ
    Scroll to Top