Sunday, 25 October 2015

አግዚአብሔር አምላክ

·       እሩቅ ነው……………………....ጥበቡ አይታወቅምና

·       ቅርብ ነው………………………ቶሎ ይሰማልና

·       መኮንን ነው………………… ቶሎ ይፈርዳልና

·       እንግዳ ነው…………..……….ቶሎ ወሬ ይሰማልና

·       ትሁት ነው………………..….ሰውን አይንቅምና

·       መሐሪ ነው ……………..…..ይቅር ይላልና

·       ባለጠጋ ነው……………..…. ለሁሉ ይመግባልና

·       ሃኪም ነው……………..…….ሁሉን በጥበብ አድርጓልና

·       ምስጉን ነው……………..…. ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሯልና

·       ረቂቅ ነው…………………… አይጨበጥምና

·       ግዙፍ ነው …………………….በዓለም ሁሉ ሞልቷልና

·       ብሩህ ነው……………………….ጨለማ የለበትምና

·       ኃያል ነው………………………የሚቋቋመው የለምና

·       እሳት ነው…………………….. ሁሉን አስፈሪ ነውና 

·        መካር ነው……………………..መጻሕፍትንና ነቢያትን እንዲሁም ሐዋርያትን ሰጥቶናልና

·       አባት ነው……………………. በፍቅር አሳድጎናልና

·       ወንድም ነው………….……. ሰው ሆኖ ወንድሞቼ ብሎናልና

·        ወዳጅ ነው……………….….. የሆዱን ሁሉ ነግሮናልና

·       አገር ነው ……………….……..እንኖርበታለንና

·       ገናና ነው…………………….. የሚቋቋመው የለምና

·       ታላቅ ነው………………….. ስፍራ አይበቃውምና

·       ጥልቅ ነው………………….. የሰው አእምሮ አይደርስበትምና

·       ፋሲካ ነው………………….. ለሁሉ ታርዷልና

·       ጨው ነው…………………... ሁሉን ያጣፍጣልና

·       እንግዳ አይደለም………… ከጥንት የነበረ ዘላለምም የሚኖር ነውና

 

 

No comments:

Post a Comment