Sunday, 20 December 2015

ክርስትናና ወጣትነት/ክፍል ሁለት/


   በቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን        

 ባለፈዉ ዝግጅት በወጣትነት በቤተ ክርስቲያን ስንኖር ልንይዛቸው የሚገቡ መንፈሳዊ ሀብታት ምን እንደሆኑ በየተራ ለመመልከት ቀጠሮ ይዘን ነበር።ዛሬ የመጀመሪያዉን ክፍል እነሆ።

            1-ዓላማ

        ወደ ሰንበት ት/ቤት ስትመጣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትቀርብ የተለያየ ዓላማ ይዘህ ሊሆን ይችላል።ጽድቅ መንግሥተ ሰማያት የሚለው የክርስትና ጉዞ ፍፃሜ ለጊዜው አይታይህ ይሆናል። እያደር ግን መብሰል  ጉዞህን በዓላማ ማድረግ ይገባሃል።ጥሩ ድራማ ተሰርቶ ለሕዝብ የቀረበ ዕለት፣ በመድረክ ላይ የሚቀርበውን ዝግጅት ለማየት ብቻ ሰ/ት/ቤት ብትገባ።በዚያም ተማርከህ ድራማውን ሲተውኑ እንደነበሩት ወጣቶች ለመሆን የሰንበት ት/ቤት አባል ሆነህ ብትመዘገብ። ለጊዜው አይደንቅም።ምክንያቱም ባየኸው ዝግጅት በመሳብህ ጊዜያዊ  ዓላማህ አባል ሆኖ ሌሎችን ያደነቅህበትን መድረክ አግኝተህ  መደነቅ ሊሆን ይችላልና ነው።ዘማሪው በመድረክ ሲዘምር ሕዝቡም የእርሱን መዝሙር  ተከትሎ ሲያሸበሽብ አይትህም ዘማሪ ለመሆን ወደ ቤተክርስቲያን ልትቀርብ ትችላለህ።በሰባክያን የስብከት መርሐ ግብር የሚሰበሰበው ሕዝብና የሚያደንቃቸውን ምዕመን ተመልክተህም ወጣት ሰባኪ ለመሆን ተመኝተህ ይሆናል።ባህታዊ ስትመለከት ብህትውና፣መነኩሴ ስታይ ምንኩሰና፣ በቄስ መስቀል ስትባረክ ክህነት /ዲቁና ፣ቅስና /፣ታይቶህ ይሆናል።በቤተክርስቲያን አካባቢ  ስላሉ አገልጋዮች ብለህ እነርሱ የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ብቻ መንፈሳዊ ብትሆን ለጊዜው አይደንቅም።ይህ አካሄድ ስህተት ቢሆንም በብዙ የወጣቶች ሕይወት ውስጥ የሚታይ የስሜት ጉዞ ነው።

         የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ከተለያየ ግብር ሲጠራቸው እርሱን የተከተሉት ማን እንደሆነ ተረድተው ብቻ አልነበረም ። የያዕቆብና የዩሐንስ እናት “ረሲ ሊተ ይንብሩ እሉ ደቂቅየ ክልኤሆሙ አሐዱ በየማንክ ወአሐዱ በፀጋምከ በመንግስትከ። እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ በመንግስትህ አንዱ በቀኝህ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ አድርግልኝ ያለችውም ለዚህ ነው/ማቴ 20-20/።በኢየሩሳሌም ሲነግስ ልጆቿን ግራዝማች ቀኝ አዝማች እንዲያደርግላት ሽታ ነው። ጌታችን ለዚህ ልመናዋ የመለሰላት መልስ “ኢተእምሩ ዘትስእሉ።የምትለምኑትን አታውቁም።”የሚል ነው። ምክንያቱም የእርሱ መንግሥት በመስቀል ላይ ስለሆነ በግራና በቀኝ ካንተ ጋር ይሁኑ ማለት በግራና በቀኝ በቀራንዮ ይሰቀል ብሎ መጠየቅ ነበርና ነው።
  

                 ያዕቆብን ዮሐንስን በእናታቸው በኩል ላቀረቡት ለዚህ ሥጋዊ ጥያቄ በተለያየ ጊዜ መልስ ተሰጥቷቸዋል።በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ፣አሳይቶ ሰማያዊ ንጉስ እንጂ ምድራዊ ንጉስ አለመሆኑን አስረድቷቸዋል/ማቴ 17-1/።በጌቴሴማኒ በምሴተ ሐሙስም ንግስናው በመስቀል ላይ መሆኑን አብረውት ሆነው እንዲረዱ አድርጓቸዋል/ሉቃ 22-39/።ሌሎችም ደቀ መዛሙርቱ ከርደተ መንፈስ ቅዱስ በፊት ከመካከላችን ታላቅ ማነው በሚል እርስ በእርስ ተነጋግረዋል።ድውይ  ፈወስን አጋንንት አወጣን ብለው በመደሰታቸውም ስማችሁ በሰማይ መዝገብ ሰለተጻፈ ደስ ይበላችሁ እንጂ አጋንንትን ስላወጣችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ የተባሉበትም ጊዜም አለ። ለጊዜው የተጠሩበትን እስኪያስተወሉት ያስደስታቸው የነበረው ምድራዊ ክብር ብቻ ነበር።ጌታችንን ተከትለው የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ሲመለከቱ፣በጾምና በጸሎት ጸንተው በፀጋ መንፈስ ሲጎበኙ ግን ይህ ሁሉ ቀርቶላቸዋል። ፍሩሃን የነበሩ ጥቡዐን ሆነዋል።ቀድሞ ያልተገለጠላቸው ምስጢር እያደር ተገልጦላቸዋል።
              መንፈሳዊ ሕይወት እንደዚህ ነው አመጣጣችን ከየትም ይሁን ከየት የመጣንበት ዓላማም የተቃናም ይሁን የተንጋደደ እያደር ግን መብሰል ያስፈልጋል።ትላንት ያስደስተን የነበረው በመድረክ ቆመን መዘመራችን፣መስበካችን፣ድራማ መሥራታችን መንፈሳዊ መባላችን፣ በጎረቤት በቤተሰብ ጾመኛ ናት፣ጸሎተኛ ናት፣የቀራት ገዳም የለም ፣ቆራቢ ነው መባላችን ይሆናል። ዛሬ ግን ሊያስደስተን የሚገባው የክርስትና ጉዞአችን ፍጻሜ የሆነው መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ መጠራታችን በእመቤታችን ምልጃ በቅዱሳን እርዳታ በገነት ለመኖር መጠራታችን ሊሆን ይገባል።
            አንዳንድ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመቀማት የመጡም ተመልሰው መንፈሳዊ ይሆናሉ።ለዘረፋ መጥተው ባህታዊ የሚሆኑ አሉ፡፡አንጣዎስ አሞራዊ የቤተ መቅደስ ገንዘብ ሲቀማ ይኖራል።ከዕለታት አንድ ቀን እንደ ልማዱ እቀማለሁ ብሎ ሲሄድ መላእክት ተገልጠው እሳት አዝንመውበታል። ሐፀ እሳት ኩናተ እሳት እየወረወሩ ወጉትም ይላል። በዚህ ምክንያት ይህ ሰው ከጥፋቱ አምኗል ተጠምቋል።/በሰማእትነትም አርፏል/ማር ይስሐቅ ገጽ 55፣ስንክሳር ነሐሴ 17/።ቅዱስ ጳውሎስ ሳውል ተብሎ ሲጠራ ሳለ ጌታችንን አሰቅሎ ፣ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ አስቀጥቅጦ ይህ አልበቃ ብሎት ሌሎች ደቀመዛሙርትን ለማሳደድ ወደ ደማስቆ ተጓዘ ። ለፈሪሳዊያን ሕግ ቀንቶ በሐዋርያት ላይ ሰይፉን መዘዘ።በዚህ ጊዜ ነው በመንገድ ጌታችን ተገልጦ ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ? የመጊያውን ብረት ብትቃወም ባንተ ይብስብሃል ያለው።ይህ  የጌታችን ተግሳፅ አሳዳጅ የነበረውን ተሳዳጅ ፈሪሳዊውን ክርስቲያን አድርጎታል /ሐዋ 9-1/።እነዚህ በርቀት ከክርስትናው ውጭ የነበሩ አበው በእግዚአብሔር ቸርነት እውነታውን ተረድተው ከተመለሱ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለህ አንተማ የመጣህበትን ጊዜያዊ ዓላማ ትተህ ለዘላቂው ዓላማ /ለገነት ለመንግሥተ ሰማያት/ የማትዘጋጅበት ምክንያት አይኖርም።    

            እንደ ሐዋርያት ለጊዜው ያልተረዳኸው ጉዳይ ቢኖር እንኳ የኋላ ኋላ መንፈሳዊውን ሕይወትን መሻቱ ካለህ መንፈሳዊ መሆንን ገንዘብ ማድረግ አይከብድህም።በመንፈሳዊ ሕይወት እየበሰልክ ጊዜያዊውን ትተህ ዘለዓለማዊውን እያሰብህ ካልሄድህ ግን ክርስትናህ ለአደጋ የተጋለጠ ይሆናል።ሁል ጊዜ ወተት የምትመኝ ጥሬ ወደ መቆርጠሙ የማትደርስ ፣ሁል ጊዜ ለዝናና ለክብር የምትሮጥ፣ ሰማያዊውን ሕይወት የማትናፍቅ ከሆነ ግን ጉዞህ አጠያያቂ መሆኑ የማይቀር ነው። ቅዱስ  ጳውሎስ የገላትያንን ምዕመናን ከዕለት ዕለት አልሻሻል ከትናንት ዛሬ አልቀየር ቢሉት ወቅሶአቸዋል። “ኦ አብዳን ሰብአ ገላትያ መኑ አሕመመክሙ ከመ ኢትእመኑ በጽድቅ ዘያስተርኢ ለዐይን ኢየሱስ ክርስቶስ።እናንተ ዐላዋቆች የገላትያ ሰዎች በምታዩት በአማናዊዉ መሢህ በክርስቶስ እንዳታምኑ ማን ተመቀኛችሁ።ዘአቅደመ ተጽሕፎ በእንቲአሁ።እንዲወለድ አስቀድሞ የተነገረለት።ከመሂ ይሰቀል።እንዲሰቀልም/የተነገረለት/” ብሏቸዋል/ገላ 3-1/።

            ከዚህ አንፃር  በጉዞህ ዓላማ ሊኖርህ ይገባል።የትላንቱን ትተህ ዛሬን በመሻሻል ስለ ክርስትና ጉዞ ፍጻሜ ማሰብ ይኖርብሀል።  አንድ ሰው ዲያቆን ቢሆን ቄስም ቢሆን ዘማሪም ቢሆን ሰባኪም ቢሆን ይህ የክርስትናው ፍጻሜ አይደለም። እነዚህ ሁሉ በክርስትና ጉዞ የሚያገኛቸው ነገሮች ናቸው ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያደርገውን ጉዞ ለማቅናት የሚያግዙት መንፈሳዊ ሥጦታዎች ናቸው።እነዚህን ይዞ በመንፈሳዊነት ከበረታ ለክብር የበቃል።አስተውል አንተም ሥጦታህን አክብረህ ፀጋህን አውቀህ በአገልግሎት ከበረታህ በመንፈሳዊነት ከፀናህ በመጨረሻ ለገነት ለመንግሥተ ሰማያት ክብር ትበቃለህ።አለበለዚያ ግን ፀጋህን ካላወቅህበት የትኛውንም ያህል ብታገለግል ከወቀሳ አትድንም።
            በወንጌል “እግዚኦ እግዚኦ በስምከ ተነበይነ ፣ወበስመ ዚአከ ወአጋንንተ አዉጻእነ ፣ወበስመ ዚአከ ኃይላተ ብዙኀ ገበርነ ይብሉኒ። በይእቲ ጊዜ እብሎሙ ግሙራ ኢየአምረክሙ ረሀቁ እምኔየ  ኩልክሙ እለ ትገብሩ ዐመፃ” “አቤቱ አቤቱ በስምህ ትንቢት ተናግረን፣ በስምህ አጋንንት አውጥተን በስምህ ብዙ ተአምራትን አድርገን አልነበረምን ይሉኛል።ያን ጊዜም ፈጽሞ አላውቃችሁም ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ/ማቴ 7-22/ ተብሎ ተጽፏል። ከዚህ ምዕራፍ ለአገልግሎት ተብሎ የሚሰጥ ፀጋ ብቻውን ለመንግሥተ ሰማያት ክብር እንደማያበቃ እንረዳለን።ለመንግሥተ ሰማያት ክብር የምትበቃው ከሁሉ አስቀድመህ ጽድቁን የምትሻ ከሆነ ነው። ሲነጋና ሲመሽ፣ስትተኛና ስትነሳ፣ስትቆርብም ንስሐ ስትገባ፣ስትዘምርም ስትሰብክም ፣ሰንበት ተማሪ ስትሆንም፣ በዓውደ ምሕረት ጉባኤ ስትገኝም በየትኛውም መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ፍፃሜህን የምታስብ ከሆነ ነው።

                ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ “ሰማዕታት ከዐው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግሥተ ሰማያት።ሰማዕታት ስለ እግዚአብሔር ደማቸውን አፈሰሱ ሰለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ/ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ/ይላል።የሰማዕታት የተጋድሎ ፍፃሜ፣የባሕታዊያን የብሕትውና ኑሮ ተስፋ፣የሊቃነ ጳጳሳት፣ የመነኮሳት፣የቀሳውስት፣የዲያቆናት፣የምዕመናን ሁሉ መንፈሳዊ ሕይወት ዳርቻ መንግሥተ ሰማያት ናት።በአንደኛውም በሦስተኛውም በስድስት በዘጠኝ በአስራ አንድ ሰዓት የገባው ሁሉ የሚቀበላት አንድ ቢኖር መንግሥተ ሰማያት ናት።

                                                             ይቆየን

Sunday, 6 December 2015

ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 2


5:- ወእቀውም ዮም በትህትና ወበ ፍቅር በዛቲ ዕለት ቅድመ ዝንቱ ምስጢር ግሩም: ዮምና በዛቲ ዕለት አንድ ወገን: ቀድሶ ያቆረበባት ቀን ናት: እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደናቁኝ ልናቃቸው ሳልል በፍቅር በትህትና ጸንቼ ግሩም በሚሆን በስጋው በደሙ ፊት እቆማለው::
ሐተታ:- ስጋው ደሙን ምስጢር አለው ከአምስቱ አዕማደ ምስጢር አንዱ ምስጢረ ቁርባን ነውና:: አንድም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት በልሳነ ነፍስ ያናግራልና:አንድም ሲለወጥ አይታይምና: ለበቁትም ሰዎች ስንኳ ከተለወጠ በኋላ ነው እንጂ ሲለወጥ አይታይምና: አንድም የወድያኛውን ምስጢር ይገልጣልና ግሩም አለ: በሚገባ ቢቀበሉት ግሩም ጸጋ ያሰጣልና: በሚገባ ባይቀበሉት ግሩም ፍዳ ያመጣልና: አንድም ግሩማን መላእክት ከበውት ይቆማሉና አንድም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት ግሩም ምስጢርን ይገልጻልና: አንድም የአምላክ ስጋ የአምላክ ደም አይገርም ማን ይገረም: አንድም የሚወደድ ሲል ነው: ኢትርዓይ ግርማ ርእየቱ ለኤልያብ እንዲል አንድም ልዩ ሲል ነው: ግሩም ምክሩ እመጓለ እመ ህያው እንዲል::

ወቅድመ ዝንቱ ማዕድ ወቁርባን ዐ ማእድም ያለው ስጋው ደሙ ነው: ሐተታ:- ማእድ አለው ማእድ ስጋዊን ከበው እንዲመገቡት ይህንም አእሩግ ህጻናት ከበው ይቀበሉታልና: አንድም ለማእድ ስጋዊ ሰው እንዲመረጥለት ለዚህም የበቃና ያልበቃ ይመረጥለታልና አንድም ማዕደ ነፍስ ነውና ቁርባን እንዳለፈው: አንድም ማእድ ጻህል ጽዋው ቁርባን ስጋው ደሙ ነው ::

6:- በአማን ቁርባን ውዕቱ ዘእይክሉ ይጥዐሙ እምኔሁ ግሙናነ መንፈስ ልቦናቸውን ሰውነታቸውን በሃጥያት ያሳደፉ ሰዎች ሊቀበሉት የማይገባቸው መለኮት የተዋሃደው እውነተኛ ቁርባን ነው:

ሐተታ:- ማን ይከለክላቸዋል ቢሉ ራሳቸው ፈርደው ይከለከላሉና አንድም ቄሱ ይከለክላቸዋልና አንድም እግዚአብሔር በምልዓት በልቡናቸው አድረው ይከለክላቸዋልና: ህዝቡ ያልበቁ ልዑካኑ የበቁ የሆኑ እንደሆነ የህዝቡን ለልዑካኑ ይደርብላቸዋል: ልዑካኑ ያልበቁ ህዝቡ የበቁ ይሆኑ እንደሆነ የልዑካኑን ለህዝቡ ይደርብላቸዋል ህዝቡም ልዑካኑም ያልበቁም የሆኑ እንደሆነ መልአክ ወስዶ በበርረሃ ለወደቁ ባህታውያን ያቀብላቸዋል: ምግብ ሁኑአቸው የሚኖር ቅሉ ይህ ነው: ያም አያውቅም ይህም አያውቅም ያ እንዳይታበይ ይህ ከቀቢጸ ተስፋ እንዳይደርስ ነው::

አኮ ከመ መስዋእቶሙ ለቀደምት አበው ዘበደመ በግዕ ሐርጌ ወላህም:: በደመ በግዕ በደመ ላህም የቀደሙ ሰዎች ይሰውት እንደነበረ መስዋእት አይደለም: አንድም የቀደሙ ሰዎች በደመ ላህም በደመ በግዕ ይሰዉት እንደነበረ መስዋዕት አይደለም::

ሐተታ:-ሃርጌን ለበግ የቀጸሉ እንደሆነ ሙክት በላህም የቀጸሉ እንደሆነ ጊድር ማለት ነው::

7:- አላ እሳት ውዕቱ:: መለኮት የተዋሃደው ቁርባን ነው እንጂ እሳት መለኮት የተዋሃደው ቁርባን ነው እንጂ:እሳት ማህየዊ ለርቱአነ ልብ ለዕለ ይገብሩ ፈቃዶ:: ለና ለ አንድ ወገን እሳትም ብዬ ብላችሁ አንድነቱን ሶስትነቱን አውቀው ህማሙን ሞቱን አምነው ሃጥያታቸውን ለመምህረ ንስሓ ነግረው መምህረ ንስሃ ያዘዘውን ሰርተው በሚገባ ለሚቀበሉ ሰዎች የሚያድን እሳት ነው::
ሐተታ:- እሳት በመጠን የሞቁት እንደሆነ የበሉት የጠጡትን ያስማማል: ደዌ ይከፍላል: ይህም ከሃጥያት ነጽቶ ቢቀበሉት ይህወተ ስጋ ህይወተ ነፍስ ይሆናል: ደዌ ነፍስ ያርቃልና::
እሳት በላዒ ለአማጽያን ለእለ ይክህዱ ስሞ:: ለና ለ አንድ ወገን ነው እሳት ማህየዊም ብላችሁ ስመ አምላክነቱን ለሚክዱ ሰዎች የሚያቃጥል እሳት ነው::

ሐተታ:- ስመ አምላክነቱን ከካዱ የማን ስጋ የማን ደም ብለው ይቀበሉታል ቢሉ ስመ ቁርባንነቱን ለሚክዱ ሰዎች::
ሐተታ:- ስመ ቁርባንነቱንስ ከካዱ ምን ይረባናል ምን ይጠቅመናል ብለው ይቀበሉታል ቢሉ በግብሩ መካድ አለና::ከሃጥያት ሳይነጹ ቢቀበሉት በፍዳ ላይ ፍዳ የሚያመጣ ስለሆነ እሳት ነበልባሉ ከወረደው ፍህሙ ከመረተው ቀርበው ያለመጠን ቢሞቁት ያቃጥላል ይህም በማይገባ ቢቀበሉት ፍዳ ያመጣልና:: ወይእዜኒ ዘበልዖ ለዝንቱ ህብስት: ወዘሰትዮ ለዝንቱ ጽዋ እንዘ እይደልዎ ደይኖ ወመቅሰፍቶ በልዓ ለርእሱ መንሱትኬ ነሢአ ሥጋሁ በድፍረት ወተመጥዎ ደሙ ዘእንበለ ሃፍረት እንዘቦ ላዕሌሁ ነውረ ሃጥያት እንዲል::ከዚህም ስጋውን ከእሳተ ባቢሎን ደሙን ከማየ ግብጽ ምሳሌ አምጥተው ይናገራሉ: እሳተ ባቢሎን ሰልስቱ ደቂቅን ሳይነካ በአፍአ ያሉ የባቢሎንን ሰዎች አቃጥሎአቸዋል ስጋውም ከሃጥያት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከሃጥያት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና ማየ ግብጽ በግብጻውያን ሲለወጥባቸው በእስራኤል አልተለወጠባቸውም ደሙም ከሃጥያት ነጽተው የሚቀበሉትን ያድናቸዋል ከሃጥያት ሳይነጹ የሚቀበሉትን ያጠፋቸዋልና ዛሬም ቀሳውስት ይህን ምሳሌ ይዘው የበደላችሁትን ሳትክሱ የቀማችሁትን ሳትመልሱ ከሃጡያት ሳትነጹ ሳትበቁ ብትቀበሉት ሥጋው ደሙ በነፍስ በስጋ ያስፈርድባችኋል እያሉ አዋጅ ይነግሩበታል::

8:-በአማን እሳት ውዕቱ ዘኢይክሉ ለኪፎቶ እሳታውያን እለ ነደ እሳት እሙንቱ ኪሩቤል ወሱራፌል ከእሳት ከነፋስ የተፈጠሩ ኪሩቤል ሱራፌል ሊይዙት የማይቻላቸው መለኮት የተዋሃደው እውነተኛ ቁርባን ነው ተፈጥሮዋቸው ከእሳት ከነፋስ ነውና:: ወሶበ ኢያእኮትኮ ለዘፈጠርከ እምነፋስ ወነድ ፈጠረ ህየንቴከ ሰንአ ዘማሬ እማይ ወእመሬት እንዲል::
ሐተታ:- ከእለተ ሰሉስ አስቀድሞስ ግብር እም ግብር የተፈጠረ ፍጥረት የለም: የመላእክትም ተፈጥሮ እምሃበ አልቦ ነው: ግብራቸውን ሲያይ እሳት ነፋስ ሃያላን ረቂቃን ፈጣኖች ፈጻሚያነ ፈቃድ ናቸው: መላእክትም ሃያላን ረቂቃን ናቸውና: ለተልኮ ይፋጠናሉና: የፈጣሪያቸውን ፈቃድ ይፈጽማሉና::
ሐተታ:- እሳት ሰብዓ ሰዶምን ደቂቀ ቆሬን አጥፍቷል ነፋስም ብእሲት ዘማን ጥቅመ ሰናኦርን ሃራ ጰራግሞንን አጥፍቷልና አንድም የባለሟልነት ስማቸው ነው: እገሌ ነደ እሳት ባለሟል ነው እንዲሉ::
ታሪክ:- ዘኢይክሉ ለኪፎቶ አለ ንጉሱ ዖዝያን ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ይባላል በቀኙ ይቀመጣል: ምነው በቀኜ ትቀመጥብኛለህ ይለዋል ወካህን ይነብር በየማነ ንጉሥ እንጂ ይለኛል ይለዋል:: ከልብሰ መግስቱ ልብሰ ክህነቱ ይበልጣል ምነው ከኔ የበለጠ ልብስ ትለብሳለህ ይለዋል ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ እንጂ ይለኛል ይለዋል:: ፍርዱን ይገስበታል ምነው ፍርዴን ትገስብኛል ይለዋል እምነ መንግስት የአቢ ክህነት እንጂ ይለኛል ይለዋል አድርጎ ቤተ መንግስትም እያረካከሰ ቤተ ክህነትን እያነጋገሰ እየጠቃቀሰ ቢያውከው በዚያም በዚያም ቢሉ ቀንቶበት ከቤተ መንግስትማ ቤተ ክህነት ከበለጠ እኔስ ባባቴ ከቤተ መንግስት ብወለድ በናቴ ከቤተ ክህነት እውለድ የለምን ብሎ ማእጠንተ ወርቁን ይዞ ልብሰ ተክህኖውን ለብሶ ሊያጥን ገባ: ሲያጥን ጢሱ ቢያርፍበት ከግንባሩ ለምጽ ተቀረጸበት በሻሽ ሸፈነው: ከሻሹ ላይ ወጣበት ለምጻሙን በእስራኤል ስንኳንስ በቤተ መቅደስ በከተማ አያኖሩትምና: እሱን አውጥተው ልጁን አንግሰዋል በዘመኑ የነበረ ነቢይ ኢሣያስ ነው ፈርቶ ሳይገስጸው ቢቀር ለምጽ ወቶበት ሃብተ ትንቢት ተነስቶት 3 አመት ከመንፈቅ ያህል ኖሯል ወእምዝ በዓመተ ሞተ ዖዝያን ንጉስ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር እንዘ ይነብር ዲበ መንበሩ ብሩህ ወነዋህ እንዲል: ዖዚያን በሞተበት ወራት ጌታ በመንበረ ጸባኦት እንዳለ ሆኖ ለኢሳያስ ታየው ያ ታፍረው ታከብረው የነበረው ንጉስ ሞተ አልፈ እኔ ግን እልፈት ውላጤ የለብኝም ሲል ሊያድነው ቢሻ መነ እፌኑ ሃበ ህዝብየ እስራኤል ሁሉ ራሱ ጠበቀ አንገቱን ቀበረ ወደወገኖቼ ወደ እስራኤል በመምህርነት ማንን ልስደድ አለ:: እስመ ማዕከለ ህዝብ ዘርኩስ ከናፍሪሆሙ ሃሎኩ አነ እስራኤል ለምጽ ይጸየፋሉ: ደግሞም ትንቢት ተነስቶብኛል እንጂ እኔ አልፈራም ነበር አለው: ወተፈነወ አሃዱ እምሱራፌል ወነስአ ፍህመ በጉጠት ወአልከፎ ከናፍሪሁ ወይቤ አእተትኩ ለከ ሃጥያተከ እንዲል መልአኩን ከአለመ መላእክት ፍህሙን በጉጠት ወስደህ አጉርሰው አለው:: ሃጥያተከ ቢል ለምጹን አራቅሁልህ ሃጥያትከ ቢል ትንቢቱን መለስኩልህ ሲል ነው:: 
ከዚህ በኋላ ለምጹ ድኖለት ትንቢቱ ተመልሶለት እንደገና አስተምሯልና: ይህም ምሳሌ ነው መልአኩ የቀሳውስት ጉጠት የስልጣነ እግዚአብሄር እሳያስ የምእመናን ለምጽ የፍዳ የመርገም ፍህም የስጋ ወደሙ :: አንድም ከናፍረ ኢሳያስ የምእመናን መልአኩ የዲያቆን ጉጠት የእርፈ መስቀል ፍህም የደሙ ምሳሌ:: መላእክት ስጋውን ደሙን የሚይዙበት ስልጣን የላቸውምና: ዘኢይክሉ አለ: ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት የሚያሰኘው ቅሉ ይሄ ነው: አባ መቃርዮስ እንዳየው ስለ ንጽህናው መልአኩ የቄሱን እጅ ይዞ ለማርቆስ ዘዮናኒ ግብጻዊ ሲያቀብለው አይቷል::

9:- ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ: ኦ ቃለ አክብሮ ቃለ አህስሮ ቃለ አራህርሆ ይሆናል: ቃል አክብሮ ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ ብሎ የሚያመጣው ነው: ቃለ አራህርሆ ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ቃለ አህስሮ ኦ ሃናንያ ኦ አብዳን ሰብአ ገላትያ ነው:: በእንተዝ ያለፈውን አጠፈ እንደገና ብሎ መጽሃፍ ያለፈውንም የሚመጣውንም ማጠፍ ልማድ ነውና የሚመጣውን አጠፈ እመቤታችን ሆይ እናከብርሻለን እናገንሻለን::
ሐተታ:- እኛ እሷን የምናከብራት የምናገናት ሆነን አይደለም ክብርሽን ገናንነትሽን እንናገራለን ሲል ነው::
እስመ ወልድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ህይወት ዘበአማን:: እውነተኛውን ምግብ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና ስላስገኘሽልን::
ሐተታ:- ዘበአማን አለ ከመስዋዕተ ኦሪት ሲለይ ያ ስጋዊ ይህ መንፈሳዊ ያ አፍአዊ ይህ ውሳጣዊ ያ ምድራዊ ይህ ሰማያዊ ነውና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ጥዋት በልቶ ለማታ ማታ በልቶ ለጠዋት ያሻል ይህ ግን በሚገባ ከተቀበሉት በሃጥያት ካላሳደፉት ህማሙን ሞቱን ለማዘከር ነው እንጂአንድ ግዜ ከተቀበሉት በሌላ ግዜ አያሻምና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ሃሰር ይሆንል ይለወጥል በሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና አንድም የዚህ አለም ምግብ ሞትን ያስከትላል ይህ ግን የዘላለም ህይወት ይሆናል አንድም ከማናዊት እመቤታችን ስለተገኘ መብልአ ጽድቅ ዘበአማን ውስቴ ህይወት ዘበአማን አለ:: ይቆየን .......ቸር ያቆየን!!!!!!

ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 1


1:- አኮቴተ ቁርባን ዘእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘደርሰ በመንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሃገረ ብህንሳ ጸሎታ ወበረከታ የሃሉ ምስለ ኩሎሙ ህዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን ::

ሕርያቆስ ማለት ህሩይ ማለት ነው : ለሹመት መርጠውታልና: አንድም ረቂቅ ማለት ነው ምሥጢረ ሥላሴን ይናገራልና : ከሊቃውንትስ ምሥጢረ ሥልሴን የማይናገር የለም ብሎ ከሁሉ ይልቅ እሱ አምልቶ አስፍቶ አጉልቶ ይናገራልና አንድም ፀሐይ ማለት ነው: አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስቅዱስ ፀሐይ ብሎ ጽፏልና : አንድም ብርሃን ማለት ነው: የምዕመናንን ልቦና በትምህርቱ ብሩህ ያደርጋልና : ዘአብርሃ መንበረ ማርቆስ በብርሃን እንዲል :አንድም ንብ ማለት ነው: ንብ የማይቀምሰው አበባ የለመ እሱም የማይጠቅሰው ሊቅ የለም:ይህም እንደምን ነው ቢሉ:ሐዋርያት የተማረ ግብረ ገብ ይሾም ብለው ሥራት ሰርተዋል: ይህስ አይደለም ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ አይገኝም ብሎ የተማረ ከሆነ ይሾም ብለዋል:: በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ብለው ግብረ ገብም ከሆነ ይሾም ብለዋል:በጸሎቱ ይጠብቃል: በትሩፋቱ ያጸድቃል:ትምህርቱን ውሎ አድሮ ያደርገዋልና ብለው ሾሙት :ይህም አባ ህርያቆስ ያልተማረ ግብረ ገብ ነው :ቢማርም ለጸሎት ለቅዳሴ ያህል ነበር:በብህንሳ በ10000 መነኮሳት በ10000 መነኮሳይያት ተሹሟል በብዙም መሾም ልማድ ነው::

አባ ሆርና አባ ኤስድሮስ በ1000 አባ አሞን በ3000 አባ ጳኩሚስ በ6000 አባ ሰራብዮን በ10000 ተሾሙ:ይህችም ብህንሳ ቅድመ ትሰይም አርጋድያ ወድህረ መኑፍ ይላል: ብዙ ግዜ ስመ ተፋልሶ አግኝቷታል :በፊት አርጋድያ ኋላም መኑፍ ተብላለች ዛሬም ብህንሳ ትባላለች:ሴትና ወንድ ያልተለየባት ገዳም ናት:እንደ ዘጌ እንደ ቆራጣ እንደ ቀንጠፋሜ እርሱም ግብረ ገብ ነውና ሥራት ቢያጸናባቸው ይጣሉታል:ያልተማረ ነውና ይንቁታል:: ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ ከመሾም መማር አይቀድምምን እያሉ; እሱ ግን ወእቀውም ዮም በትህትና ወበፍቅር ብሎ እንዲያመጣው: እንደጠሉኝ ልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር እና በትህትና ጸንቶ ያስተምራቸው ነበር::

ከዕለታት ባንዳቸው በምን ምክንያት እንሻረው አሉ:ቀድሰህ አቁርበን ብለን በዚህ ምክንያት እንሻረው ብለው መክረው ቀድሰህ አቁርበን አሉት: የሱ ግን ተምኔቱ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤቴ ምስጋና እንደባህር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ በዝቶልኝ እንደምግብ ተመግበው እንደ መጠጥ ጠጥቼው እንደ ልብስ ለብሼው እያለ ይመኝ ነበር:ቅዳሴ ገብቶ ሥርዓቱን ጨርሶ ከፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ ከሊቃውንት ቅዳሴ የሚያስቸግር የማንን እናውጣለት እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ የለመኗትን የማትነሳ የነገሯትን የማትረሳ እመቤት ገልጻለት ጐሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ ብሎ ወይእዜኒ ንሰብሐ እስኪል ድረስ ሰተት አድርጎ ተናግሮታል: የሚንቁት የሚጠሉት ይህ የነገሩትን ቀለም እንኳን አከናውኖ መናገር የማይችል ዛሬስ እንግዳ ድርሰት እደርሳለው ብሎ አገኝ አጣውን የቆጥ የባጡን ይቀባጥራል: ብለው አደነቁበት የሚወዱት የሚያከብሩት ከመንፈስቅዱስ ነው እንጂ እንዲ ያለ ምሥጢር ከእሩቅ ብዕሲ ይገኛልን ብለው አደነቁለት: ወዲያው የሚወዱት የሚያከብሩት ጽፈን ደጉሰን አንይዘውምን አሉ: የሚንቁት የሚጠሉት ደግሞ ማን ተናገረው ብለን እንይዘዋለን አሉ እንደ ሊማዱ አድርገን አንይዘውም አሉ:: ለሃገራቸው እንግዳ ድርሰት የተደረሰ እንደሆነ ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ይጥሉታል: ከእሳት ደህና የወጣ እንደሆነ ከውሃ ይጥሉታል ከውሃ የወጣ እንደሆነ ከህሙም ላይ ይጥሉታል ድውይ የፈወሰ እንደሆነ ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ይይዙታል::

ይህንንም ቅዳሴ ማርያም ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ላይ ጣሉት ከእሳት ደህና ወጣ: ከውሃ ጣሉት ከውሃ ደህና ወጣ: ከህሙም ላይ ጣሉት ድውይ ፈወሰ: ይልቁንም ሙት አስነስቷል:: ደገኛ ድርሰት ነው ብለው ጽፈው ደጉሰው ይዘውታል:በጥራዝም 14ኛ አድርገው ጠርዘውታል: ከ14ቱ ቅዳሴም ተአምራት ያልተደረገበት የለም: የቀደሰበት ምን ቀን ነው ቢሉ: ከእመቤታችን ከ 33ቱ በዓላት ባንዱ ቀን ነው: አንድ ባህታዊ ከባለሟልነት የተነሳ ከ33ቱ በዓላት ማንን ትወጃለሽ ብሎ እመቤታችንን ጠየቃት:ኪዳነምህረትን ልደታን አስተርአዮን ፍልሰታን አለችው: ከሊህ ከ4ቱስ ማንን ትወጃለሽ ቢላት ከጸባብ ወደ ሰፊ: ከጨለማ ወደ ብርሃን: የወጣውበት ነውና ልደቴን እወዳለው አለችው: ቀድሞ እነ ሳልወለድ እናትና አባቴን መባችሁን አንቀበልም ብለው አዝነው ተክዘው ነበር: የነሱ ሃዘን ሃዘኔ ነውና እነን ከወለዱ በኋላ መባቸውን ተቀብለዋቸው ደስ ብሎዋቸዋል: የነሱ ደስታ ደስታዬ ነውና እንዳለችው የልደታ እለት ነው የቀደሰው:: እሱስ ማንን ሊቀድስ ኖሯል ቢሉ ከቅዳሴ ሐዋርያት ሌላ አያቅም ነበርና ቅዳሴ ሐዋርያትን: ይህስ አይደለም ለእመቤታችን ቅዳሴ ሐዋርያት ምኗ ነው: ምን ቢቸግር ተበድሮ ጋሬዳ እንዲሉ ቅዳሴ እግዚእን ሊቀድስ ነበር ስሟን ባያነሳ እምድንግል ተወሊዶ ከመ ፈቃድከ ይፈጽም ብሎ በምሥጢር ያነሳታል::

ከባህር ወዲህስ ማን አምጥቶልናል ቢሉቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ መደባይ ታብር በሚባል ቦታ ይኖር ነበር እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ አባ ሕርያቆስን ከብህንሳ በደመና ጠቅሳ ያረድ ካለበት አድርሳ አንተ ውዳሴየን አንተ ቅዳሴየን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ ብላቸው እነሱም ነግረውት በዜማ አድርሶታል:: ከዚሁ አያይዞ 13ቱንም ቅዳሴ በዜማ ደርሷል: ይህም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል::ከተከዜስ ወዲህ ማን አምጥቶልናል ቢሉ ሳሙኤል ትውልደ ጌዴዎን ዘገበዘ አክሱም ይለዋል እሱ አምጥቶልናል እሱም ይሄን እየደገመ ሲሄድ ክንድ ከስንዝር ከመረት መጥቆ ይሄድ ነበር: ከዕለታትም በአንዳቸው ውሃውን ቢባርከው ህብስት ሆኖለት ተመግቦ ምዕመናንን መግቧቸዋል:: እመቤታችንም የፍቅር ምልክት ሁለት ንዋያት ሰታዋለች ነጭ እጣን እና እንቁ ነው: ከዛም አያይዛ ውዳሴየን ከቅዳሴዬ ጋራ አንድ አድርጎ የሚደግመውን ሰው አንተ ከገባህበት ውሳጤ መንጦላዕት አገባዋለው:ብላ ተስፋውን ነግራዋለች:: ይሀውም ሊታወቅ ዛሬ በዋልድባ ያጠና በቃሉ: ያላጠና በመጽሃፍ ቅዳሴ ማርያም ሳይደግም የሚውል የለም:ይህም ተስፋ ውዳሴዋን ከቅዳሴዋ ጋር አንድ አድርጎ ለምደግም ሰው ሁሉ ነው:እንጂ ለሱ ብቻ አይደለም:ዳንድ ባህታዊ ከምስጋናሽ ሁሉ ማንን ትወጃለሽ ብሎ ቢጠይቃት ልጄ ዳዊትን አቡነ ዘበሰማያትን ቢደግሙለት እንዲወድ እኔም ውዳሴዬን ቅዳሴዬን ቢደግሙልኝ ወዳለው ብላዋለች ::
አባ ሕርያቆስ ተሹሞ ሳለ ብዙ ድርሳንን ደርሷል ብዙ ተግሳጽ ጽፏል ከብዙውም አንዱ ይህ ቅዳሴ ነው እረፍቱ በጥቅምት 2 ነው:: 

ልመናዋ ክብሯ በኛ ይደርብንና ህብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ አክብሮ ለውጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ደመ ወለደ እግዚአብሔር በሚያደርግበት ግዜ በብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ የተሾመ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት እመቤታችንን ያመሰገነበት ምስጋና ይህ ነው:: ቁርባን ቀሳውስት ሥጋውን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርገው ወደ መንበር የሚያቀርቡበት አኰተት የሚለውጡት የሚያከብሩት አንድም በክብር በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ አንድም ቁርባን የሚቀበሉት የሚያቀብሉት አኰተት የሚለውጡት የሚያከብሩት ልመናው ክብሩ በኛ ይደርብንና በብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ የተሾመ አባ ሕርያቆስ በመንፈስቅዱስ ተገልጾለት የተናገረው ቅዳሴ ይህ ነው: ጸሎታ ወበረከታ ቢል ተመስጋኝቱን ሲያይ: ክብሯ ልመናዋ ይደርብንና ጸሎቱ ወበረከቱ ቢል አመስጋኙን ሲያይ ነው::

2:- ይ:ካ: እግዚአብሔር ምስለ ኰልክሙ ቄሱ:-እግዚአብሄር በሁላችሁም አድሮባችሁ ይኑር ይበል::
ይ:ሕ: ምስለ መንፈስከ ህዝቡም እንደቃልህ ይደረግልን ይበሉ::
ይ:ካ: አእኩትዎ ለአምላክነ :-ቄሱ ፈጣርያችንን አመስግኑት ይበል
ይ:ሕ: ርቱዕ ይደሉ :- ህዝቡም ዕውነት ነው ይገባል ይበሉ
ይ:ካ: ብነ ሃበ እግዚአብሔር አምላክነ 
ህዝቡም በፈጣርያችን በእግዚአብሄር ዘንድ ዋጋ አለን ይበሉ::

3:- መጽሃፍ ከመጽሃፍ ማያያዝ ልማድ ነው: አባቷ ዳዊት ለንጉሰ ሰማይ ወምድር ምስጋና ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ ብሎ ተናግሮ ነበርና እሱም ለንግስተ ሰማይ ወምድር ምስጋና ላቅርብ ባለ ግዜ ጐሥዐ አለ አንድም ለአባቷ ለዳዊት የገለጸ መንፈስቅዱስ ምሥጢር ከምስጢር አያይዞለት ጐሥዐ አለ ወአየድዕ ይላል በልብ መደብ ቁሞ ወአነ አየድዕ ይላል በቃለ መደብ ቁሞ ልቦናዬ በጎ ነገርን አውጥቶ ተናገረ:: አንድም ልቦናየ ስንቡል መንፈስቅዱስን ተቀብሎ በጎ ነገርን ገሳ ሐተታ:-በሃገራቸው የተመገቡት ምግብ ያልተስማማቸው እንደሆነ ዑድ ሰንደል የሚባል ሽቱ አለ ያንን ተመግበው በጎ በጎ ነገር ገሣው ይላሉና ያጎሥዓኒ እንዲል ትግሬ
ሐተታ:- ሶስት ግዜ ጐሥዐ ጐሥዐ ጐሥዐ ብሎ መላልሶ ተናገረ ስለምን ቢሉ በንጽሃ ስጋ በንጽሃ ነፍስ በንጽሃ ልቦና መዓረግ አምሳል አንድም ወጣንያን ማዕከላውያንን ፍጹማን የሚያመሰግኗት ስለሆነ: አንድም በዚህ አለም በገነት በመንግስሠማያት ያሉ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ስለሆነ: ከዚህስ አስቀድሞ መንግስተ ሰማይ የገባ የለም ብሎ ኋላ መንግስተ ሰማያት የሚገቡ ጻድቃን የሚያመሰግኗት ሲለሆነ: አንድም ሊቃውንት በሚስጥረ ሥላሴ መጀመር ልማዳቸው ነው: ሦስት ግዜ ደጋግሞ መናገሩ የሦስትነት: ቃሉ አለመለወጡ የአንድነት:ምሳሌ ነው:አንድም ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ የሚል ነውና ሦስት አርዕስት ተናገረ ለሦስቱም ያመጣል::

4:-ወአነ አየድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም:- አባቷ ዳዊት ወአነ አየድዕ ግብርየ ለንጉሥ ብሎ ነበርና ለዚያ ዋዌ እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው አለ ሐተታ:- መጀመርያ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ አለ በቅድስና ወበንጽህና ስርጉት አንቲ የሚል ነውና ለዚያ አርዕስት ነው::

አኮ በአብዝኖ በማብዛት አይደለም : አላ በአውህዶ በማሳነስ ነው እንጂ ሐተታ:-የእመቤታችን ምስጋና ከምስጋና ቢበዛ እንጂ ያንሳልን? መትህተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን አይደለችምን ቢሉ እውነት ነው የእመቤታችን ምስጋና ሰማይና ምድር ብራና አብህርት ቀለም ዕጽው ብርዕ አዕባን መድመድ: መላዕክት ደቂቀ አዳም ጸሃፍት ቢሆኑ ባልተፈጸመም ነበር:እንደቅድስናዋ እንደንጽህናዋ አይደለም ሲል እንዲህ አለ ከዚያ ሁሉ ቅዱስ ቄርሎስ የቴዎዶስዮስን እህቶች የአርቃድያ የመሪናን ምስጋናቸውን ተናግሮ ዝውዳሴንዘተናገርነ ይውህደ እምክብርክን እንዳለ አንድም ንባብን በማብዛት ምሥጢሩን በማሳነስ አይደለም: ንባቡን በማሳነስ ምሥጢሩን በማብዛት ነው እንጂ::

ወአነ አይድዕ ውዳሴሃ ለድንግል:- እኔም የእመቤታችንን ምስጋና እናገራለው ሐተታ:-ሁለተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ድንግል አኮ ስፋጣን ዘናዘዙኪ አላ መላእክተ ሰማይ ሐወጹኪ በከመ ተብህለ ካህናት ወሊቃነ ካህናት ወደሱኪ የሚል ነውና::

አኮ በአንሆ በቃለ ዝንጋዔ:- ዝንጋዔን የሚያመጣ ዝንጋዔን የሚያስከትል ነገርን በማብዛት አይደለም: ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ: ብዙ ቢተቹ ይሰለቹ:እንዲሉ ነገር ከበዛ ዘንድ ከምን ተነስቶ ከዚህ ደረሰ ይባላልና ነው::
አላ በአሕፅሮ:-በማሳጠር በመጠቅለል ነው እንጂ ሲሰበር ይሰንጠር ሲረዝም ይጠር እንዲሉ:

ወአነ አየድዕ ዕበያቲሃ ለድንግል:- የድንልን ገናንነቷን እናገራለው ሐተታ:- ሦስተኛ ጐሥዐ ብሎ ነበርና ለዚያ ህዳግ ይህስ ለራሱ አርእስት ነው ብሎ ኦ ማርያም ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ብሎ የሚያመጣ ነውና: ይህስ አይደለም አርዕስት ተቀዳደመ ለፊተኛው አርቆ ለኋለኛው አቅርቦ አይሰጥም ብሎ መጽአ ሃቤኪ ቃል ብሎ የሚያመጣ ነውና:: ወአነ አየድዕ ውዳሴሃ : ወአነ አይድዕ ቅዳሴሃ : ወአነ አይድዕ ዕበያቲሃ ብሎ ሦስት ጊዜ መላልዞ ተናገረ::
ኦ ማርያም በእንትዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ ኦ ድንግል ምልዕተ ውዳሴ: ኦ ድንግል አኮ ዘተአምሪ ርስሃተ የሚል ነውና: አንድም አባቷ ዳዊት ቀደሰ ማህደሮ ልዕል:መሰረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን እስመ ሓረያ እግዚአብሄር ለጽዮን ብሎ ሦስት ግዜ መላልሶ አመስግኗታል:: ይቆየን የዚህ ክፍል ሁለት ነገ ይቀጥላል ..............ችቸር ያቆየን!!!!!

Thursday, 3 December 2015

ክርስትናና ወጣትነት/ክፍል አንድ/

በቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን

  ሰላሌ ሃገረ ስብከት እያለሁ ነዉ።አስታውሳለሁ። ወረዳ ላይ ለአገልግሎት ስወጣየሚያጥመኝ የሚገርምኝም ነገር ነበር።የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ሳስተምር ከመካከላቸው ሁል ጊዜ አንድ አዛውንት አያለሁ። ወጣ ካለ ቦታ ከገጠር ነው የሚመጡት። ብርቱ የሆነ መንፈሳዊ ስሜት አላቸው። በአካባቢያቸው ብዙ ጨሌአቃጥለዋል። በዛ ያሉ ምዕመናንም ለንሰሓ አብቅተዋል። ለገጠሩ ሕብረተሰብ ጥሩ አርበኛናቸው። እኒህ አረጋዊ ጉባኤ ሲያበቃ ይጠራቀሙትንአንድ መድበል ጥያቄ ይዘው ይመጣሉ።ከዚያ በቃመጽሓፍ ቅዱስ እየገለጡ መጠየቅ ነው።መናፍቃንንአጥብቀው ስለሚቃወሙ ለእነርሱ የሚሆን መልስበጉንጫቸው አለ።                

          ታድያብዙጊዜየሚናገሩትነገርነበር።እንደውእድሜንወደኋላመመለስአይቻልምእንጂምነውበተቻለናበመለስኩት፣ በእኛጊዜየሃይማኖትትምህርትእንዲህስላልተስፋፋባተሌሆነንነውየኖርነውይላሉ።እናንተታድላችኋልዕድሜያችሁንእየተጠቀማችሁበትነውበማለትበቁጭትይናገራሉ።መዝሙርሲዘመር፣ስብከትሲሰበክ፣ሰንበትት/ቤት ድራማሲሰራ በቃ እርሳቸው ከራሳቸው ጋር ይሟገታሉ።እድሜ ከንቱ ሳላውቀው ሄደና በቃ ወጣትነቴአመለጠኝ ማለት የዘወትር ተግባራቸው ነው።

           አንድቀንመከርኳቸውመንፈሳዊቅናትመቅናታቸውመልካምቢሆንምለቀቢፀተስፋእንዳይዳርጋቸውይተዉ።የእርስዎየጥሪዕድሜይሄከሆነስልሳኛአመትዎንምእንደሃያናሰላሳይቆጥርልዎታልይልቅስባልዎትዕድሜእየተጠቀሙይበርቱብዪአጽናናኋቸው።በወጣቱእንቅስቃሴየሚገረሙምዕመናንይህንይላሉ።ምነዉዳግመኛበተፈጠርኩ፣ምነውወጣትነቴንበድጋሚባገኘሁትይላሉ።ግንአይሆንምዕድሜከነጎደነጎደነው።ከመፀፀትአንዷንዲናር/መንግሥተሰማያትን/ዋጋቸውሆናለመቀበልበገቡበትሰአትገብተውታማኝሆነውድራሻቸውንቢወጡመልካምነው።የሦስተኛውም፣የስድስተኛውም፣የዘጠነኛውም፣ሰአትዋጋአንድዲናርነው።

           ዕድሜሳይሰሩበትያለፈባቸውእንዲህእንዲጽናኑእየመከርንወጣትነትበእጃችንያለግንብዙይጠበቅብናል።ዛሬንእንደቀልድባተሌሆነንካሳለፍነውነገመጸጸትእንድሚመጣመዘንጋትየለብንም።ወጣትነታችንጥሎንሳይሄድእያንዳንዱንደቂቃሰከንድእንዳይባክንአድርገንማሳለፍይጠበቅብናል።ዕድሜበላያችንሳይሮጥእኛበእድሜእንሩጥ።ጊዜንእየገደልነውሳይሆንእየተጠቀምንበትእንዲያልፍእናድርግ።ለሌላውንብረታችንከምንሳሳውበላይለዕድሜእንሳሳ።መክሊቱንቀብሮያለትርፍእንደተገኘውሰነፍባሪያየተሰጠንንጊዜሳናተርፍበትባለቤቱእንዳይመጣብንእንጠንቀቅ።

           ለመጸለይዓይኔን፣ለመስገድወገቤን፣ለመፆምአቅሜንየማንልበትዕድሜወጣትነትነው።ከልብከተነሳንበዚህዕድሜበፈጣሪእርዳታብዙመስራትእንችላለን።ለአገልግሎትከአንዱስፍራወደአንዱብንሮጥ፣ገዳማቱንበየሥፍራውዞረንብንሳለም፣አበውንለመርዳትገንዘብብናወጣ፣ብንረዳ፣መንፈሳዊማህበርብንመሰርትሁሉምይቻላል።ጉልበትን።ገንዘብን፣እውቀትን፣ሁሉንምበስራለማዋልየሚመቸውበዚህዕድሜነው።

          የመናፍቃንንተንኮልለመከላከልዘመኑንዋጅተንመልስማዘጋጀትየምንችልበትእድሜወጣትነትነው።በየዋህነትየኮበለለውን ምዕመንወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ በአፍበመጽሐፍ የምንልበት ሃይማኖታችንን ለመጠበቅሌትና ቀን የምንደክምበት ዕድሜ ወጣትነትነው።በዚህ ዕድሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነገረ መለኮትንአርቅቆ አምጥቆ እንደጻፈ / ዮሐ 21-24 /አትናቴዎስ የሃይማኖት ጸሎትን ከሦስት መቶ አስራስምንት ሊቃውንት ጋር በመሆን እንዳረቀቀ አንርሳ።

          ሰማዕትነትቢመጣአንገትንለሰይፍለስለት፣ሰውነትንለሞትለመስጠትየሚታገሱበትዕድሜወጣትነትነው።ስለቤተክርስቲያንሕይወትንእንኳንዋጋአድርጎለመስጠትይህዕድሜይመቻል።ቀዳሜሰማዕትቅዱስእስጢፋኖስየአይሁድንቁጣሳይፈራእውነትንመስክሮበሰማዕትነትያረፈውበእዚህእድሜመሆኑንምአንዘንጋው።ሊቀሰማዕታትቅዱስጊዮርጊስበዐላውያንነገሥታትፊትስለአምላኩመስክሮየገጠመውንመከራሁሉበጽናትየተቀበለውገናበሃያሦስትዓመቱነው።ከቅዱሳትአንስትቅድስትአርሴማንየመሳሰሉእናቶችመከራንስለሃይማኖታቸውየተቀበሉትበዚህእድሜነው።

          ከዚህሁሉአንጻርበወጣትነትየዕድሜክልልያለንቤተክርስቲያንንበጽናትበትጋትማገልገልይጠበቅብናል።ዕድሜያችንለመንፈሳዊነትየሚመችእንደመሆኑእንጠቀምበት።በጉብዝናችንወራትፈጣሪያችንንማሰብእንዳለብንአንዘንጋ።/መጽ መክ12-1/ ውድ የሆነዉን የዕድሜ ክልላችንንለእግዚአብሔር አንንፈገው።ይልቁንም ከእጁየተቀበልነዉን እድሜ ፣ጤና ….መልሰን ለፈጣሪእንስጠው።ጤናችን ፣ጉልበታችን ፣ገንዘባችን ሁሉየእርሱ ነው።የእኛ የሆነ አንዳች ነገርየለንም።ሌላው ቀርቶ እኛም እራሳችን የእርሱነን።ይህንን ሳንረሳ ሁል ጊዜ ለፈጣሪ ታማኝ እንሁን።

         ወደፊትበዚህዓምድወጣቱበቤተክርስቲያንእንዴትመመላለስእንዳለበት፣መንፈሳዊለመሆንምንማድረግእንዳለበትበሰፊውእንመለከታለን።የሚገጥሙትንምፈተናዎችበጊዜዉናበሰዓቱእንዳስሳለን።ለአሁኑይቆየን።

የብሕትውና(የምንኩስና) ኑሮ – ክፍል 2


2. የሥርዓተ ምንኩስና ታሪክ

 2.1   - አባ ጳውሊ  እና  አባ እንጦንስ

    2.1.1-  አባ ጳውሊ

አባ ጳውሊ  እና  አባ እንጦንስ

አባ ጳውሊ  እና  አባ እንጦንስ

በተባሕትዎ መኖር ከጥንት ዘመን የመጣ ይሁንእንጂ የብሕትውናን ኑሮ ሥርዓት በወጣለት መልኩየጀመረው አባ ጳውሊ የተባለው ግብፃዊ አባት ነው፡፡በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት በክርስቲያኖችላይ በተነሣው ስደት ምክንያት አባ ጳውሊና ቆይቶምደግሞ ሌሎች የአካባቢው ክርስቲያኖች በግብፅበረሃዎች ውስጥ በምናኔ ይኖሩ ነበር፡፡

ይህንን አባ ጳውሊ የጀመረውን ሥርዓት አጠናክሮለማስፋፋት ያበቃው ደግሞ አባታችን አባ እንጦንስነው (251-356ዓ.ም.)፡፡

  2.1.2- አባ እንጦንስ

አባ እንጦንስ ግብፅ ውስጥ ቆማ በተባለች መንደርከሀብታም ቤተሰቦች በ251 ዓ.ም ተወለደ፡፡ወዳጆቹገና የ2ዐ ዓመት ወጣት እያለ ስላረፉበማቴ.19÷21 ላይ ያለውን ትምህርት መሠረትአድርጐ የወረሰውን ሀብት በሙሉ በመሸጥለድኾች አከፋፈለና ወደ ግብፅ በረሃ በመውረድለ85 ዓመት በተጋድሎ ኖሯል፡፡

የአባ እንጦንስ ዓላማ ከሰው ርቆ በብሕትውናበበረሃለመኖር ነበር፡፡ ነገር ግን ተአምራቱን የሰማውሕዝብ ከግብፅ ብቻ ሳይሆን ከመካከለኛውምሥራቅና ከአውሮፖ ምድር ሳይቀር ወደ በአቱይጐርፍ ጀመር፡፡ በኋላም በሕይወቱ የተማረኩባሕታውያን በዙሪያው ባሉ ዋሻዎች መኖር ጀመሩ፡፡

የአባ እንጦንስን የሕይወት ታሪክ የጻፈለት አባታችንአትናቴዎስ ሲሆን አትናቴዎስም ሥርዓተ ምንኩስናንየተቀበለው ከዚሁ አባት ነው፡፡ ታላቁ ንጉሥቆስጠንጢኖስም ዝናውን በመስማቱ «በጸሎትህአስበኝ» በማለት ደብዳቤ ጽፎለት እንደነበር ታሪኩይናገራል፡፡

አባ እንጦንስ ለ85 ዓመታት በብሕትውና ሲኖርከበኣቱ የወጣው ሁለት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡የመጀመሪያው በንጉሥ መክስምያኖስ ትእዛዝስደትና መከራ የደረሰባቸውን ክርስቲያኖችንለማፅናናት በመላዋ ግብፅ በ311 ዓ.ም. ያደረገውጉዞ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አርዮሳውያን በቅዱስአትናቴዎስ ላይ በተነሡበትጊዜ ለመንፈስ አባቱለሐዋርያዋው አትናቴዎስና ለንጽሕት ተዋሕዶእምነቱ ያለውን ቆራጥነት በመግለጥ ሕዝቡንለማጽናት በ338 ዓ.ም ደቀ መዛሙርቱን አስከትሎየተጓዘው ሐዋርያዊ ጉዞ ነው፡፡

የባሕታውያኑ በአባ እንጦንስ ዙሪያ መሰባሰብለማኅበር ጸሎት፣ ከዘራፊዎች ለመጠበቅና የደከሙአበውን ለመርዳት አስችሏቸዋል፡፡ በዚህምየመጀመሪያው የገዳማውያን የማኅበር ኑሮተጀመረ፡፡

አባ እንጦንስ የመነኮሳቱ ልብስ ነጭ ፈረጅያና ቆብ፣መታጠቂያቸውም ከቆዳ የተሠራና ሠቅ እንዲሆንወስኖ ነበር፡፡

መነኮሳቱ ሳምንቱን በየበኣታቸው ሲጾሙና ሲጸልዩሰንብተው እስከ እሑድ ምሽት ድረስ ደግሞ በአባእንጦንስ ዋሻ ዙሪያ ተሰባስበው ሲጸልዩና ሥርዓተአምልኮ ሲፈጽሙ ይውሉ ነበር፡፡ አባ እንጦንስ በዚህሁኔታ ሥርዓተ ምንኩስናን አስፋፍቶ በተወለደበ105 ዓመቱ ዐርፎአል፡፡አባ ጳውሊ የጀመረውንሥርዓተ ምንኩስና አጠናክሮ ያስፋፋው አባእንጦንስ ነው፡፡

2.2 አባ ጳኩሚስ

በሥርዓተ ምንኵስና ታሪክ ሌላውን ታላቅ ሥፍራየያዘው ደግሞ የአባ እንጦንስ ደቀ መዝሙርየነበረው አባ ጳኩሚስ ነው (23ዐ-346 ዓ.ም.)፡፡ አባጳኩሚስ ግብፅ ውስጥ ኤስና በምትባል መንደርከአረማውያን ቤተሰቦች በ29ዐ ዓ.ም. ተወለደ፡፡በቆስጠንጢኖስ ዘመነ መንግሥት ለውትድርናምተመልምሎ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በውትድርናውዘመን የክርስቲያኖችን ቆራጥነት፣ደግነትና ርኀራኄበማየቱ ልቡ ስለተነካ ግዳጁን ፈጽሞ ሲመለስበ313 ዓ.ም. የክርስትናንእምነት ጠንቅቆ በመማርአምኖ ተጠመቀ፡፡

የአባ ጳኩሚስ ልቡና የቅዱስ እንጦንስ ደቀመዝሙር በነበረው በአባ ጴላጦንስ ኑሮስለተማረከወደ በረሃ ወርዶ የብሕትውናን ኑሮናሥርዓት ሲማር ከቆየ በኋላ በ32ዐ ዓ.ም. በዓባይወንዝ አጠገብ ታቤኒስ ከተባለው ቦታ የራሱን ገዳምመሠረተ፡፡ በዙሪያው ለተሰበሰቡት መነኰሳትምየአንድነት ኑሮ ሕግ አወጣላቸው፡፡በአባ እንጦንስለተጀመረው የማኅበረ መነኰሳት ኑሮየተጠናከረሥርዓት አውጥቶ የበለጠ ከማስፋፋቱምበተጨማሪ ዘጠኝ የወንድና ሁለት የሴቶች ገዳማትመሥርቷል፡፡

ዋልድባ ገዳማውያን

አባጳኩሚስ ያወጣው የመነኰሳት የአኗኗር ሕግ ዋናውቅጂ ሲጠፋ ወደ ላቲን የተተረጐመው ግን እስከዛሬድረስ ይገኛል፡፡ ከሕግጋቱ መካከል፡-

መነኮሳት ጠዋትና ማታ በማኀበርእንዲጸልዩ፣

በኀብረት በአንድነት እንዲሠሩ፣

ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትረውእንዲመለከቱ፣

የቁም ጽሕፈት እንዲማሩ፣

ገቢና ወጪአቸው አንድ ላይ እንዲሆን፣

በአንድነት እንዲመገቡ፣

አንድ ዓይነት ልብስ እንዲኖራቸው፣

ንጽሕ ጠብቀው እንዲኖሩ፣

ደግነት፣ ፍቅርና ታዛዥነትእንዲኖራቸው፣የሚሉት ይገኙበታል፡፡

አንድ ሰው ወደ ገዳማቱ ሲመጣ የሦስት ዓመትአመክሮ ይሰጠውና ጠባዩና ፍላጐቱ ይገመገማል፡፡ከዚያ በኋላም ብርታቱና ጽናቱ ታይቶ ወደ ማኅበረመነኰሳቱ ይቀላቀላል፡፡ አባ ጳኩሚስ በዚሁ ዓይነትመንገድ ሥርዓት ሠርቶ ሕግ አጽንቶ ገዳማትንካስፋፋ በኋላ በተወለደ በ56 ዓመቱ በ346 ዓ.ም.ዐረፈ፡፡

3. ሥርዓተ ምንኵስናን በሌላው ዓለምያስፋፉ አበው

3.1 አትናቴዎስ ሐዋርያዊው (295-373 ..)

አትናቴዎስ ሐዋርያዊው

አትናቴዎስ ሐዋርያዊው

ቅዱስአትናቴዎስ ከታላቁ ርዕሰ ገዳማውያን ከአባእንጦንስ ዘንድ ሥርዓተ ምንኵስናን ተምሮፈጽሟል፡፡ የአባ እንጦንስን የሕይወት ታሪክ (ገድል)የጻፈውም እርሱ ነው፡፡ አርዮሳውያን በቅዱስአትናቴዎስ ላይ በግፍ በተነሡበት ጊዜ ወደ ሮምበመሰደድ ከ339-346 ዓ.ም. ተቀምጧል፡፡ የሮምክርስቲያኖች አትናቴዎስና ተከታዮቹ የለበሱትንየመነኰሳት ልብስና ቆብ ተመልክተውተገረሙ፡፡እርሱም በቆየባቸው ሰባት ዓመታት ከአባ እንጦንስየተማረውን የመነኰሳት ሕግና አኗኗርአስተምሯቸዋል፡፡ በሮማ ምድርም ሥርዓተምንኩስናን ለማስፋፋት የመጀመሪያው አባትአትናቴዎስ ሐዋርያዊ ነው፡፡

                        

3.2 ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ (330-379 .)

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ

ባስልዮስ በግብፅ ገዳማት በብሕትውና ከቆየ በኋላከ36ዐ ዓ.ም. ጀምሮ በታናሽ እስያ (ዛሬ ቱርክበሚባለው አካባቢ) የምነናን ኑሮ በመመሥረትዛሬየግሪክ፣ ሩሲያ፣ ወዘተ. አብያተ ክርስቲያናትየሚገለገሉበትን የመነኰሳት ሕግ ያወጣው እርሱነው፡፡

3.3 ዮሐንስ ካስያን (360-435 ..)

ግብፅ ውስጥ በቴብያድና ጥቂት ዓመታትበብሕትውና ከቆየ በኋላ ወደ ፈረንሳይ በመመለስበ415 ዓ.ም. በፈረንሳይማርሴይ አጠገብ ሁለትገዳማትን መሠረተ፡፡ በግብፅ ያጠናውን ሥርዓተመነኰሳት መሠረት አድርጐ ሁለት መጻሕፍትንምአዘጋጅቷል፡፡

እንግዲህ በዚህ ሁኔታ በአባ ጳውሊ የተጀመረውየምንኵስና ሕይወት በመላው ዓለም ሊስፋፋናወደሀገራችንም ለመድረስ በቅቷል፡፡የመጀመሪያውን የሴቶች ገዳም የመሠረተችውደግሞ የአባ ጳኩሚስ እኀት ማርያም ነች፡፡

ምንኵስና በኢትዮጵያ

ይቀጥላል - ይቆየን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዋቢ

1.    ትንሣኤ ቁ.99/1978

2.    ገድለ አባ ሊባኖስ

3.    ገድለ አባ ዮሐንስ

4.    ዜና መንዝ

5.    የአንኰበር መሳፍንት የታሪክ መጽሐፍ

6.    ትንሣኤ ቁ.11/79

7.    ትንሣኤ ቁ.22/80

8.    Conti Rossini, steria PL.XLIV

9.    ሉሌ መላኩ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አ.አ1986

10. አባ ጎርጎርዮስ፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለምመድረክ

11. አባ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንታሪ

ሐመር መጽሔት

ምንጭ: http://www.melakuezezew.info/